
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ማስረሻ በላቸው የ”ቢስት ባር” በቤንች ብሔር ዘንድ አኩሪ ፣ አቃፊ ፣ ሰላም ፣ አብሮነትና ፍቅር የሚገለጽበት ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ የአዲስ ዓመት ብስራት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ቢስት ባር ወንድማማችነት የሚሰበክበት ፣ ከሌሎች ወንድምና እህት ብሔረሰቦች ጋር አብሮ የሚያከብሩት የመተማመን ፣የመደጋገፍ ፣የመተባበር የአብሮነትና የመደመር በዓል ነው ሲሉም አቶ ማስረሻ በመልዕክታቸው አስተላልፈዋል ።
አቶ ማስረሻ በላቸው የቢስት ባር የብሔሩ ተወላጆች የመኸር ምርቶችን በጋራ የሚቀምሱበት ለአዲስ አዝመራ የሚዘጋጁበት በመሆኑ ይህንን እሴት ይበልጥ በማጠናከርና ወደ ልማት ተጠናክረው በመግባት ለምርትና ምርታማነት መትጋት እንደሚገባ በዓሉ አስተማሪ ነው ብለዋል።
በምግብ ራስን የመቻልና ከልመናና ተረጂነተ የመላቀቅ ውጥናችንን ለማሳካት እንደዚህ አይነት ክብረ በዓላት ከእርሻ ስራ ጋር ያላቸውን ተዛምዶ እና ለማዕድ ማጋራት ያለቸውን ትውፊታዊ ትርጓሜ በተገቢው ማጤን ሚናው የማይናቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
እንኳን ለቢስት ባር “የቤንች ብሔር የአዲስ ዓመት መለወጫና የምስጋና በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ ልባዊ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
