






በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የጥምቀት ከተራ በዓል በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች በድምቀት መከበር ጀምሯል።
የእምነቱ ተከታይ በሆኑ ምዕመናን እና ሌሎች አካላት በመታጀብ ታቦታቱ ከማደሪያ ስፍራቸው በመውጣት ወደ ጥምቀተ ባህር እያመሩ ይገኛሉ።
የሸካ ዞን ዋና ከተማና የክልሉ ብዝሃ ማዕከል በሆነችው ቴፒ ከተማ ታቦታቱ ከየአቅጣጫው ታጅበው በድምቀት ወደ ጥምቀተ ባህር እያመሩ ሲሆን በአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማና ማሻ ከተማ ላይም በተመሳሳይ ወደ ጥምቀተ ባህሩ እያመሩ ናቸው።
በሌሎችም የዞኑ ወረዳዎችም ታቦታቱ ወደ ጥምቀተ ባህሩ የሚገኙ ሲሆን በነገው ዕለትም የጥምቀት በዓል በድምቀት ይከበራል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበው የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።
