


በጎንደር የተመዘገቡ ስኬቶችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሰላምን ማጽናት እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ገለጹ።
ጥምቀት በጎንደር ፋሲለደስ ባህረ ጥምቀት የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች እና በርካታ ምዕመናን በታደሙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የጎንደር ከተማ የሚመጥናት የእድገት ማማ ላይ መውጣት የምትችልበት ዘመን ነው።
የጎንደር ከተማ በፈጣን እድገት ውስጥ እንድትጓዝ ሰላምን ማጽናት ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።
ሰላምን መጠበቅ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ ጨምረው ተናግረዋል።
በጎንደር የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ዳር ከማድረስ ባለፈ ጠብቆ ለትውልድ ማሻገር እንደሚገባም ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
