



ሴቶች ለሰላም፣ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እያበረከቱት ያለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች የቦንጋ ማዕከል መሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢ ወ/ሮ ሰብለፀጋ አየለ ገለጹ።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የቦንጋ ማዕከል መሠረታዊ ድርጅት የአባላት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
በመሠረታዊ ድርጅት የአባላት ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ የተግባር አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን”የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼ ምንዳን አስረክባለሁ” በሚል መሪ ቃል የመሠረታዊ ድርጅት አባላት እና አመራር ምክክር አድርጓል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የቦንጋ ማዕከል መሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢ ወ/ሮ ሰብለፀጋ አየለ በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ወቅት እንደገለጹት ሴቶች ዜጋን በመተካት፣ዜጋን በመቅረጽ እና ትውልድን በማብቃት አይተኬ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።
ሴቶች ለሰላም፣ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እያበረከቱት ያለው አስተዋፅዖ በሀገራችን ከተመዘገቡት ሁለንተናዊ ለውጦች የጎላውን ሚና እንዳላቸው ገልጸው ይህንን ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ሴቶችን በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መሠረታዊ ድርጅት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
የበለጸገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማውረስ የሴቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የመሪነት ሚናቸውን አጠናክረው ሊወጡ ይገባል ሲሉ ወ/ሮ ሰብለፀጋ አየለ ገልጸዋል።
በህዋስ እና በመሠረታዊ ድርጅት የሚጠበቅብንን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ድክመቶች ፈጥኖ ማረም ይገባል ብለዋል።
የክልሉ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ውብዓለም በዛብህ እንደገለጹት “የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼ ምንዳን አስረክባለሁ” በሚል መሪ ቃል በዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ እና በሴቶች የኢኮኖሚ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረው ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረክ የተሳካ ውይይት መካሄዱን ተናግረዋል።
የሰላም ጉዳይ የሁላችን ጉዳይ ነው ያሉት ወ/ሮ ውብዓለም የክልላችን ሰላም እና አንድነት ለማስጠበቅ ሴቶች የመሪነት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የሴቶችን ዘላቂ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት በማረጋገጥ በኩል በሊጉ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ የሚገኝ ሲሆን ይህንንም ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ሰው ተኮር እሳቤዎች የሆኑት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ ማስቀጥል፣የሌማት ትሩፋት ተግባራት ፤ምግቤን ከጓሮ ፣የደም ልገሳ መርሀ ግብር ማካሄድ፤በቦንድ ግዢ መፈፀም፤የማህፀን ጫፍ ካንሰር ግንዛቤ መፍጠር የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ከሁሉም አባላት ይጠበቃል ብለዋል።
እህትማማችነት እና ወንድማማችነት እሴት የሚጎለብት ተግባር ላይ በትብብር መንፈስ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
የሴቶች ሊግ መሠረታዊ ድርጅት አባላትና አመራር የበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ከየቀበሌው ለተውጣጡ ሴቶች ለምግብ ፍጆታ የሚሆን አበርክተዋል።
የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት በትኩረት እንደሚሰሩ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ የቦንጋ ማዕከል የመሠረታዊ ድርጅት አባላትና አመራር ከወዲሁ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዴሞክራሲና የባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ፣ የአስተዳደር ዘርፍ የመሠረታዊ ድርጅት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር መስፍን ወዳጆ ፣የኢኮኖሚ ዘርፍ የመሠረታዊ ድርጅት የፖለቲካና ርዕዮተዓለም ዘርፍ ስብሳቢ አቶ በላይ ኮጁአብ፣ ፣የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የቦንጋ ማዕከል መሠረታዊ ድርጅት የአባላትና አመራሮች ተገኝተዋል።
