በትግራይ ክልል ጦርነት አያዋጣም፦ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል አሁንም ወደሰላም መሄድ ይገባል ብለዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጨማሪ ውጊያ እንዳይነሳ የሚደነቅ ስራ ሰርቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ምርጫ እስኪደረግ ክልሉን ለአንድ ዓመት ያስተዳድራልም ብለዋል።

በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ሙሉ ለሙሉ ያልተፈፀመው የትጥቅ ማስፈታት እና መልሶ የማቋቋም ሒደት መሆኑንም ተናግረዋል።

ይህ ባለመሆኑ የትግራይ ሕዝብን በጀት ለወታደር እንዲውል አድርጓል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም በክልሉ ሰላም እንዲኖር ነው የምንፈልገው ብለዋል።

ጦርነትን ትተን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የቋጨነው ለሰላም ብለን በስምምነቱ የትግራይ ሕዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኝ የሚያስችል ጊዜያዊ አስተዳድር አቋቁመናልም ብለዋል።

በክልሉ ተፈናቃዮችን ለመመለስ የፌደራሉ መንግስት ዛሬም ዝግጁ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተፈናቃዮች ስም የሚሰራው ፖለቲካ መቆም እንዳለበት አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *