በአዕምሮ እና በስጋ መቀንጨርን ለመከላከል የምግብስርዓትና የስርዓተ ምግብ ፕሮግራሞችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባ ተገለጸ::

Spread the love

በምግብስርዓትና ስርዓተ ምግብ ፕሮግራም ዙሪያ ያተኮረ ክልል አቀፍ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ የተሳተፉ አካላት በሰጡት አስተያየት በአዕምሮ እና በስጋ መቀንጨርን ለመከላከል የምግብ ስርዓትና የስርዓተ ምግብ ፕሮግራሞችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የምግብ ስርዓትና ስርዓተ ምግብ ፕሮግራም የተጠናከረ መሆን ጤናማ እና አምራች ትውልድ እንዲኖር ያግዛል ሲሉም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የተጀመሩ የምግቤን ከጓሮዬና የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በማጠናከር በተለይም እናቶች ካመረቱት ምርት የተመጣጠነ ምግብ እንዲመገቡ ግንዛቤ የማስጨበጡ ስራ ሊጠናከር ይገባል ሲሉ የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ወጣች ጉዳይ ቢሮ ምክል ኃላፊና የሴቶችና ህጻናት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም አምሳሉ ተናግረዋል።

በክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀይሌ ዘውዴ እንደገለጹት በአዕምሮ እና በስጋ መቀንጨርን ለመከላከል የምግብስርዓትና የስርዓተ ምግብ ፕሮግራሞችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በክልሉ ከትምህርት ቤት ጀምሮ በተገቢው የምግብ እጥረት ያሉባቸውን በመለየት ድጋፍ ማድረግ ይገባል ያሉት አቶ ሀይሌ የተመጣጠነ ምግብ ባለማግኘታቸው 45 ህጻናት በክልሉ በመቀንጨር ምክንያት መሞታቸውን ጨምረው ተናግረዋል።

የብዝሃ ሴክተር የምግብ ስርዓትና የስርዓተ ምግብ አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ አስረሳሽ ሰበታ በበኩላቸው ባለፉት 6 ወራት በዘርፉ የሚበረታቱ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

በቀጣይ የተጠናከረ ስራ ለመስራት እንዲያስችልም የብዝሃ ሴክተር የምግብ ስርዓትና የስርዓተ ምግብ ካውንስል መመስረቱ ወሳኝ እንደሆነም አብራርተዋል።

በተቋማቱ መካከል ቅንጅታዊ አሰራሮች እንዲጠናከሩና ለተግባሩም ስኬት ቁርጠኝነትና ኃላፊነት የተወሰደበት ውይይት መሆኑን የገለጹት አስተባባሪዋ አስፈላጊ መረጃዎችን በማደራጀት እና ለሚመለከተው አካል ተደራሽ በማድረግ የሚገኙ ሀብቶችን ለተፈለገው ዓላማ ለማዋል የጋራ ጥረት ያስፈልጋል ብለዋል።

የክልሉ የምግብ ስርዓትና የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም የብዝሃ ሴክተር አስተባባሪና የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ አቶ ማቴዎስ ማልዳዬ ፕሮግራሙ ውጤታማ እንዲሆን ተቋማዊ የቅንጅት አሰራሮችን ማጠናከር ቅድሚ የሚሰጠው ተግባር ነው ብለዋል።

በነበረው የምግብ ስርዓትና የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም የጋራ መግባቢያ ሰነድ በመፈራረም በቀጣይ የተቀናጀ አሰራር ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።

ተግባሩን በኃላፊነትና በተጠያቂነት ለመፈጸም የሚያስችል ውይይት መደረጉን የገለጹት አቶ ማቴዎስ በክልሉ በሰቆጣ ቃል ኪዳን በሚሰሩ ስራዎች የተናበበና የተደራጀ መረጃ ሊኖር እንደሚገባም ተናግረዋል።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተደረገው የምግብ ስርዓትና የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም በክልሉ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ተረፈ ዘውዴ የማጠቃለያ መመሪያ በመስጠት ተጠናቋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *