በክልሉ በተለያየ ምክንያቶች ግንባታቸው የተጓተቱ ፕሮጀክቶች ደረጃ በደረጃ ለማጠናቀቅ ይሰራል – ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ::

Spread the love

የታርጫ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃና ሳንቴሽ ፕሮጀክት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአከባቢው ነዎሪዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

መንግሥት የዜጎችን ፍላጎት ለማሳለጥ በያዘው ቁርጠኛ አቅም ካለው ውስን ሀብት በመመደብ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ በተግባር እየፈታ ነው ያሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ ማጠናቀቅ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን መጀመር የብልጽግና ፓርቲ አይነተኛው መገለጫ ነው ስሉ ተናግረዋል።

በክልሉ በተለያየ ምክንያቶች ግንባታቸው ተቆርጦና ተጓተዉ የቆዩ ፕሮጀክቶች መኖራቸው ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግስት እነዚህን ፕሮጀክቶች ደረጃ በደረጃ ካለው ውስን ሀብት በመመደብ ህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዛሬ የተመረቀው የታርጫ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በከተማው የሚስተዋለውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ይቀርፋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ተጠቃሚው ህብረተሰብ ውሃ እንዳይባክን በሀላፊነት መጠቀም እንዳለበትና የሚመለከተው የመንግስት አካል ደግመው ከዘርፉ የሚገኘው ሀብት በጥንቃቄ ማስተዳደር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ክልሉ ስደራጅ የነበረው አጠቃላይ አማካይ የውሃ ሽፋ 32.7 ከመቶ የነበረ ቢሆንም በክልሉ መንግሥትና በሌሎች ረጂ ተቋማት በተደረገው ርብርብ አሁን ላይ ሽፋኑ 40 ከመቶ መድረሱን የክልሉ የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸው ገልጸዋል።

በዚህም ዛሬ የተመረቀውን የታርጫ ከተማ ንጹህ ወሃ መጠጥ ፕሮጀክት ጨምሮ በክልልና በፌዴራል መንግስት በረጂ ተቋማት እንዲሁም በማህበረሰብ ተሳትፎ በድምሩ 97 ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ 250 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ሌሎች አከባቢዎች አየተደረገ ያለው የውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ስጠናቀቅ የክልሉን የውሃ ሽፋን አሁን ከደረሰበት የበለጠ ከፍ እንደሚያደርግም ኃላፊው ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ከአሃዳዊ ዋሽ ሁለተኛ ምዕራፍ ፕሮግራም በተገኘ የገንዘብ ብድር እንዲሁም በክልልና በዞኑ መንግሥት የወጪ መጋራት ስረዓት የተገነባ መሆኑ ተገልጿል።

ፕሮጀክቶችን አስጀምሮ በማጠናቀቅ ሪቫን መቁረጥ ህዝብ በመንግስት ላይ ያለውን እምነት በእጅጉ እየጨመረ ነው ያሉት የዞኑ አስተዳደር አቶ ዳዊት ገበየሁ በዞኑ ያለውን አነስተኛ የውሃ ሽፋን ለማሳደግ መንግሥት በሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የታርጫ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አና ሳንቴሽን ፕሮጀክት የከተማውን ነዋሪዎች ረዥም ጊዜ የውሃ ጥያቄ የሚፈታ ነው ያሉት የውሃ ሚኒስቴር የሚኒስቴሩ ተወካይ አቶ ማሙሸት ሀይሌ ናቸዉ።

ፕሮጀክቱ ዘላቂ አግልግሎት እንዲሰጥ የውሃ ጉድጓድ ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ መጠበቅ እንዲሁም ሌሎች የውሃ መሠረተ ልማት መጠበቅ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *