


ልዩነቶች እና አለመግባባቶች በዘላቂነት እንዲፈቱ ወደ ፈጣሪ መጸለይ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ የንስሐ፣ የምልጃ እና የምስጋና መርሐ -ግብሩ በኢትዮያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እና ወደ ኃላ የማይመለስ እርቅ እንዲፈጠር የወንጌል አማኞች የሚጸልዩበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አክለውም መርሐ -ግብሩ ምዕመኑ ለሀገሪቱ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ “ጌታ እንዲረዳው” የሚማልድበት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ስር ያሉ የተለያዩ ቤተክርስቲያናት መሪዎች፣ አባቶች፣ ዘማሪያን፣ መጋቢዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
