ክልላችን ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምቹና በዘርፉ ለሚሰማራ አካላት ውጤታማ የሚያደረግ ነው-ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

Spread the love

በኢንዱስትሪ ሚኒስትር አዲሱ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲና የተኪ ምርት ስትራቴጂ ላይ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በውይይት መድረኩ እንደገለጹት ክልላችን ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምቹና በዘርፉ ለሚሰማራ አካላት ውጤታማነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

ክልሉ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በቆዳ፣በተፈጥሮና በተለያዩ በማዕድናት ዘርፍ ትልቅ ፀጋ የታደለ በመሆኑ በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልግ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገልጸዋል።

በክልላችን በመንግሥት ደረጃ የተጀመረው ንቅናቄ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በማጠናከር ተልዕኮን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራም አስገንዝበዋል።

አምራች ኢንዱስትሪው ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ገበያን ለማረጋጋት አይተኬ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

የኢፊዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በበኩላቸው ሀገሪቱ ባለፉት ጊዜያት በርካታ ሪፎሞችን አልፋለች የአምራች ኢንዱስትሪ የዚሁ ሪፎርም አካል ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የነበረ ፖሊሲ የአሁኑ ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ያላስገባ በመሆኑ አሁን ላይ ፖሊሲውን በመከለስ በኢንዱስትሪዎች ምክር ቤት መጽደቁን ተናግረዋል።

የተሻሻለው ፖሊሲው በሀገሪቱ እየተመዘገበው ያለው ለውጥ በአስተማማኝ መሠረት በመጣል ቀጣይነት እንዲኖረው ሚና የጎላ ነው ብለዋል።

እንዱስትሪው የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶችን መሳብ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠርና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካትና የወጭ ምርትን ማሳደግ ሌላኛው ተልዕኮ አድርጎ እንደሚንቀሳቀስ የገለጹት ሚኒስቴር ደኤታው በዚህም የ10 ዓመት ፖሊሲና ስትራቴጂ በመንደፍ ይሰራል ብለዋል።

ክልሉ በተፈጥሮ ዕምቅ ፀጋ የታደለ አካባቢ በመሆኑ ይህን ወደ እንዱስትሪው ማውጣት ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስቴር ዴኤታው በዚህም ኢንዲስትሪው የበኩሉን ሚና እንደሚወጣም አብራርተዋል።

የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ተካ አማካኝነት የአዲሱ አምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲና ስትራቴጂ ተኪ ምርት የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል ።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *