የቤንች ብሔር የአዲስ ዘመንና የምስጋና በዓል ቢስት ባር እየተከበረ ይገኛል

Spread the love

የቤንች ብሄር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል (ቢስት ባር)፣ የኢፌዲሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በሚዛን አማን ከተማ በድምቀት አየተከበረ ነዉ።

ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ እየተከበረ ባለው የቢስት ባር በዓል የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች፣ የብሄረሰቡ ተወላጆችና ተጋባዥ እንግዶች እየታደሙ ይገኛል።

በዓሉ በትላንትናዉ ዕለት በሸይ-ቤንች ወረዳ ዣዢ ቀበሌ በልዩ ልዩ ሁነቶች በድምቀት ስከበር መዋሉ ይታወሳል።

የበዓሉ ማጠቃለያ በዚህ ሰዓት ሚዛን አማን ከተማ፣ በአማን የቀድሞው አየር ማረፊያ ሜዳ የበዓሉ ታዳሚዎች በባህል ልብስ አሸብርቀው በልዩ ድባብ እየተከበረ ይገኛል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *