





የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቦንጋ ከተማ ልዩ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ መሠረተ ድንጋይ ለማስቀመጥ ቦንጋ ከተማ ገብተዋል፡፡
ሚኒስትሩ ቦንጋ ከተማ ሲደርሱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና ሌሎች የክልልና የካፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢው ማህበረሰብ ደማቅ አቀባበል ተደርጎባቸዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ በቦንጋ ዩንቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎች የሚጎበኙ፣ በቦንጋ ከተማ ልዩ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ መሠረተ ድንጋይ እንደሚያስቀምጡ እና በቀጣይ በክልሉ የትምህርት ስርዓቱን ማሻሻል እና ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ ምክክር ያደርገሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
