የዓድዋ ድል መታሰቢያው እስካሁን ባለመገንባቱ ያስቆጫል፦-ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ::

Spread the love

የዓድዋ ድል ከሀገርና አኅጉር ተሻግሮ በዓለም የተስተጋባ አኩሪ ድላችን ቢሆንም ይህን በአንድ ቦታ በአግባቡ የሚገልጽ የዓድዋ ድል መታሰቢያ አለመገንባቱ የሚያስቆጭ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ሣኅወርቅ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የእኛ ብቻ ሳይሆን ለነጻነት፣ ለሕዝቦች እኩልነት ተስፋን የሰጠ ድል ነው ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህን ድል ይዘን እስካሁን ታሪካችንን የሚመጥን ሥራ ባለመከናወኑ ያስቆጫል ነው ያሉት፡፡

ዛሬ ላይ የዓድዋን ድል ታሪክ በሚመጥን አግባብ መታሰቢያ መገንባቱን ጠቅሰው÷ ለዚህም ሐሳብ ከማመንጨት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደረጉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደርን አመስግነዋል፡፡

ታሪክን በቅጡ በመረዳት እንደ ዓድዋ አስተሳሳሪ እና አንድነትን የሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ መትጋት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ምናልባት የሐሳብ እና የፍላጎት ልዩነት ቢኖር እንኳ የመጀመሪያው ምርጫ ውይይት እንጂ ጠመንጃ ሊሆን እንደማይገባም ነው ያስረዱት ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *