



በፕላንና በልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር በዶ/ር ፍጹም አሰፋ የተመራ የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን በቤንች ሸኮ ዞን በደቡብ ቤንች ወረዳ ግብርና ልማት ስራ ጃንቹ የመዝ ክላስተር እርሸ፣ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አቢይ አህመድ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጦ ወደስራ የተገበውን የደንቢ ገበታ ለትውልድ የፕሮጀክት አፈፃፀም ያለበት ደረጃ እና በሌማት ትሩፋት ውጤቶችአንዱ አካል የሆነው የማር ምርት ተመልክቷል።
በደቡብ ቤንች በ200 አርሶአደሮች በራስ ተነሳሽነት እየለማ ያለው 85 ሺህ ሄክታር ማሣ ጃንቹ የመዝ ክላስተር የሙዝ እርሻ፣ በወረዳው የተለያዩ የፍራፍሬ፣ የበቆሎ ፣ የሽንኩርት እንዲሁም የሚዛን አማን አዳሪ ትምህርት ቤትን ተዘዋውረው ተመልክቷል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
