


የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ተወካይ ሳሙኤል ባይድ ዶው ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በአየር ንብረት ለውጥ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ በርካታ ሃብቶችን ማሰባሰብ እና መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
የተጀመረውን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ልማት ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በተለይ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ቴክኒካል ድጋፍ እንደሚያደርግ ተወካዩ መናገራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
