የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት ለግሉ ዘርፍ እኩል ዕድል የሚሰጥ ነው። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ

Spread the love

የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስረዓት ለግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች እኩል የመወዳደር ዕድል በመፈጠር ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ የኢፌዴሪ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ አክለው፥ አዲስ የተዘረጋው የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት በበየነ መረብ የሚከናወንና በግዥ ስርዓቱ ላይ ግልጽነት የሚፈጠር አሰራር መሆኑን ተናግረዋል።

የኤሌክትሮኒክ የግዥ የሚከናወንበት ሲስተም አስተማማኝ የደህንነት ዋስትና ያለው መሆኑን ያብራሩት ዋና ዳይሬክተሯ ህጋዊ ተጫራቾች በለማው በየነ መረብ ተመዝግቦ ያለ አንዳች ገደብ ከየትኛውም አከባቢ ሆነው በጨረታው መወዳደር እንዲወዳደሩ ዕድል የሚፈጠር መሆኑን ጠቁመዋል።

ሲስተሙ በአስካሁኑ ሂደት በፌዴራል ተቋማት ተግባራዊ ተደርጎ ውጤታማ መሆኑን ያብራሩት ወ/ሮ መሠረት በቀጣይ በክልሎችም ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት፣ የሰው ሀይል፣ የሲስተም ዝርጋታ እና የቴክኖሎጂ ቁሳቁስ ማሟላት ተግባር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ በቀጣይ በ10 የክልል ተቋማት ስርዓቱን ተግባራዊ እንዲያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ወደ ተግባር እንዲገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ለማሳለጥ የሚረዱ የመሠረተ ልማት አውታር የማሟላት ተግባርን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቅርብ ክትትል እንዲደግፍ የጠየቁት ርዕሰ መስተዳድሩ በ2018 በተሟላ መልኩ ሁሉንም የክልል ተቋማት ወደ ሲስተም ለማስገባት ይሰራል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊ የባለድርሻ አካላት በበኩላቸው፥ ለተግባሩ ውጤታማነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ በማንሳት ድጋፋዊ ክትትሉ እንዲጠናከር ጠይቀዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *