በሎስ አንጀለስ ሰነድ አልባ ነዋሪዎችን ማሰር በመጀመሩ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ብሔራዊ ዘባቸውን ወደ አካባቢው አዘመቱ

Spread the love

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 2ሺህ የብሔራዊ ዘብ ጠባቂዎችን ወደ ሎስ አንጀለስ አሰማርተዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያደረጉት ሰነድ አልባ ነዋሪዎችን የማሰር ዘመቻን ተከትሎ ለተነሳው ተቃውሞ ምላሽ ነው።

የአካባቢው ባለስልጣናት ተቃውሞውን መቋቋም ተስኗቸዋል ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፥ የፌደራል መንግስት ችግሩን መፍታት ባለበት መንገድ ይፈታልም ብለዋል።

የካሊፎርኒያ ስቴት ገዥ የሆኑት ጋቪን ኒውሶም የትራምፕ ርምጃ ውጥረቶችን እንደሚያባብስ ተናግረዋል። “ይህ የተሳሳተ ተልእኮ ነው የህዝብ አመኔታም ይሸረሽራል” ብለዋል ገዥው።

በከተማው ዙሪያ በሚደረጉ ሕገ ወጥ ነዋሪዎችን የመያዝ ዘመቻዎች በርካቶች መታሰራቸውን ተከትሎ፤ ተቃዋሚዎች በከተማው መሐል በሚገኘው የፌደራል ህንጻ አቅራቢያ ተሰብስበው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር።

ሰልፉ የቀጠለ ሲሆን፥ ሕዝቡን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ እና ሌሎች አማራጮችን የጸጥታ ኃይሎች ወስደዋል፤ የተወሰኑ ተቃዋሚዎችም ታስረዋል።

አንድ ከፍተኛ የጸጥታ ኃይል አባል ለሲኤንኤን እንደተናገሩት፤ የብሔራዊ ዘብ ጥበቃን ማሰማራቱ ከልክ በላይ የሆነ ምላሽ ነው ብለዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *