ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ በጀሙ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል

Spread the love

መጋቢት 28/2018 ዓ.ም በምዕራብ ኦሞ ዞን በሀገራችን መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም እውን የሆነውን ሀገራዊ ለውጥ 8ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል።

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ለውጡ እውን ከሆነ ወዲህ የተመዘገቡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በዚህም ድምጻችን ለብልጽግና ለሠላም እና ለፍትህ፤ በመጋቢት 24 ፍሬ ወደ ተምሳሌታዊ ጉዞ፣ ጠንካራ መሠረት የተምሳሌትነት ጉዞ ስንቅ፣ መሠረት ባለው እርምጃ ወደ ተምሳሌትነት፣ መጋቢት 24 የተምሳሌታዊነታችን መሰረትና መፍለቂያ ነው፣ የመጋቢት 24 ፍሬዎች የተምሳሌትነት ጉዞ የትውልድ ብልፅግና እና የመሳሰሉት መፈክሮችን አሰምተዋል።

በባለፉት ዓመታት በፈተና ውስጥ የጸናች በስኬት የደመቀ ኢትዮጵያን ገንብተናል፤ መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ለውጥ መነሻና ብልጽግና መሠረት ነው፣ መጋቢት 24 በመስዋዕትነት የመጣ በመስዋዕትነት እንጠብቀዋለን ብለዋል።

በድጋፍ ሰልፉ የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የጀሙ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የመንግስት ሠራተኞች እየተሳተፉ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *