በሰሜን ቤንች ወረዳ በወረዳው የዘንድሮው የ2017 ዓ/ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ጌንጃ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል

Spread the love

በሰሜን ቤንች ወረዳ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ 2966.25 ሄክታር መሬት እንደሚለማ ተገለፀ

በይፋ ማስጀመሪያ ስነስርዓቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የሰሜን ቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስንታየሁ በፍቃዱ ሠውና ተፈጥሮ ተቻችለው እና ተከባብረው መኖር ከቻሉም በጠራራ ጸሀይ ዝናብ ይመጣል ሲሉም ተናግረዋል።

የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ቀድሞ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረ እና ቀጣይነት ያለው የአፈርና ውሃ ጥበቃን በማሳደግ የአፈር ለምነትን የምንጨምርበት እንድሁም አፈርን ማከም ተፈጥሮን ለኑሮ ምቹና የተሻለ የሚያደረግ ነው ተብለዋል።

በዚህም ተፋሰስ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን አብራርተዋል ።

የዘንድሮው ተፋሰስ ልማት ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠት በስነ አካላዊ እና ስነ ህይወታዊ ስራዎች እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ይህንንም ውጤታማ ለማድረግ በወረዳው በተለያዩ አደረጃጀቶች በዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ስራ 72,794 የሰው ሀይል እንደሚሳተፍ ገልጸዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ባህል ቱሪዝም ስፖርት መምርያ ሀላፊና የወረዳው ደጋፊ አመራር አቶ ጌታቸው ኮይካ የተጎዱ መሬቶችን በተፋሰስ ልማት በማልማት መልሶ የማዳን ስራ መስራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል ።

በዚህም ደርቀው የነበሩ በርካታ ምንጮች መመለስ ጀምረዋል የተጎዱ መሬቶች አገግመዋል ብለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ፣የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት በአትክልት ልማት ዘርፍ አመራሩ፣ባለሙያው እና አርሶአደሮች ተቀናጅተው በመስራት ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚገባቸው አሳስበዋል ።

የሰሜን ቤንች ወረዳ የግብርና አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አማኑኤል ንጉሴ በበኩላቸው የተቀናጀ የተፋሰስ ስራ ለበርካታ አመታት በወረዳው ሲተገበር መቆየቱን ተናግረው በዘንድሮው አመት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በወረዳው በ21ዱም ቀበሌዎች በ21 ተፋሰሶች 2966.25 ሄክታር መሬት እንደሚለማ እና በዚህም ጎንለጎን ያረጀ ቡና ጉንደላ ተግባራትና የነቀላ እንደሚከናወን በዚህ መርሀ ግብር 724794 አ/አደሮች እንደሚሳተፉ ተናግረዋል ።

በዕለቱም የተሳተፉ አርሶአደሮች ከዚህ ቀደም በተሰራው ስራ ተጨባጭ ለውጥ ማየት በመቻላቸው ዘንድሮም በተደራጀ መንገድ በመፈጸም አካባቢያቸውን ለማልማት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *