የአየር ወለድ ትምህርት ቤት የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላትን በአየር ወለድነት አሰልጥኖ አስመረቀ

Spread the love

በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ የአየር ወለድ ትምህርት ቤት የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር ሠልጣኞችን በአየር ወለድነት አሰልጥኖ አስመርቋል።

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ለተመራቂ የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላት የአየር ወለድ ልዩ ምልክት የሆነውን የደረት ክንፍ አልብሰዋል።

የአየር ወለድ ስልጠና የወሰዱት የክፍሉ አባላት ቀደም ብለው እጅግ ፈታኝና ውስብስብ የሆነ የልዩ ሀይል ፀረ- ሽብር ስልጠና መውሰዳቸውንም አስታውቀዋል።

የክፍሉ አባላት የአየር ወለድ ስልጠናን በተጨማሪነት መሰልጠን አስፈላጊና ወሳኝ በመሆኑ ስልጠና መሰጠቱን መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላት በግልም ሆነ በቡድን የሚሰጣቸውን ውስብስብና ልዩ ግዳጅ መወጣት የሚያስችላቸው አቅም እንዲኖራቸው ተደርገው በላቀ ደረጃ መሰልጠናቸውን ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ገልጸዋል።

ተመራቂዎችም የሀገሪቱ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የዜጎቿን ህይወት የመቀየር ልማታዊ ጉዞ እንዳይደናቀፍ የተዘጋጁበትን ልዩ ግዳጅ በፍፁም ዲሲፕሊንና ፅናት ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *