በግማሽ ዓመቱ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል፡፡ የክልሉ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2017 ግማሽ ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ የዕቅድ አፈጻጸም የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት እና የማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ተገምግሟል።

በግምገማው ላይ ባለፉት 6 ወራት በክልላችን በተሰሩ የልማት ስራዎች ተከናውነው የተሻሉ አፈጻጸሞች መኖራቸውን ያህል ትኩረት የሚሹና በቀጣይ የሚሰሩ ጉዳዮች መኖራቸውን የመድረኩ ተሳታፊ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተናግረዋል ።

በመድረኩ የተሳተፉ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ቀጣይ ትኩረት በሚሹ በተላይ ከግብርና አኳያ ገበያን ሊያረጋጋ የሚያስችል በቂ ምርት ከማምረት፣ የማዕድን ሀብት አስተዳደር እንዲሁም ህገወጥ ንግድና ግብይ መከላከል እንደሚገባ አንስተዋል።

የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የንግድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አምዴ ፋሪስ የክልላችንን ያለውን ፀጋ መሠረት በማድረግ የታቀዱ ዕቅዶቻችን ተግባራዊ በማድረግ ባለፉት 6 ወራት በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወን መቻላቸውን የተገመገመበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አብዲዮ መኮንን በበኩላቸው እንደ ክልል ህዝብን በማስተባበር የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ከዳር ለማድረስ መድረኮችን በመፍጠር የበጀት ዓመቱን ግማሽ አፈፃፀም በጋራ መገምገም ጥንካሬዎቻችንንና ድክመቶቻችንን በመለየት ያሉንን አቅሞች በውል በመገንዘብ የጋራ አስተሳሰብ ለመፍጠር ያገዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መድረኩ የታችኛው መዋቅር አመራር ተግባራትን በተሻለ ደረጃ ለማከናወን እንዲያግዝና ድጋፉን እንዲጠናከር ለመሄድ ለአመራሩ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ኃላፊዋ ወ/ሮ ብርቅነሽ ሻንቆ እንደ ሀገር ከተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ሀገር የሚትፈልገውን ተልዕኮ ለማሳካት በክልላችን ያሉትን ዕድሎቻችን ውስጥ ምን ያህሉን አሳክተናዋል፣ ምንስ ጉድለቶች አሉብን የሚለውን በመገምገም በቀሪዎቹ 6 ወራት ውጤታማ ለመሆን በሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ በሰፊው ውይይት የተደረገበት መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

በቀጣይ በክልሉ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የማህበረሰብን ንቃተ ህልና በማሳደግ አቅርቦት ላይ ያለውን ችግር መቅረፍና ተቀናጅቶ በጋራ መስራት ከተቻለ ክልሉን በሀገር አቀፍ ደረጀ ማስጠራት የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት መፈፀም ይቻላል ነው ያሉት ወ/ሮ ብርቅነሽ ሻንቆ፡

ይህ የግምገማ መድረኩ ከተግባሩ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው የከተማ አስተዳደር የዞን አስተባባሪ አካላት ያሳተፈ በመሆኑ ከወትሮው ለየት ያለነው ያሉት የክልሉ ግብርና ቢሮ የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ፣ ከዚህም መነሻ በጥንካሬና በጉድለት የሚነሱ ቀጣይ ለማሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መድረክ መሆኑን አንስተው ይህም ሂደት መቀጠል እንደለበትም ገልፀዋል ፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የተሻለ ቢሆንም ከክልሉ ካለው እምቅ አቅምና የማልማት ፍላጎት አኳያ ገና ብዙ መሠረት የሚጠይቅ ነው ለዚህም በቀጣይ የተሻለ ለመከናወን በጋራ ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ ይጠበቃልም ብለዋል፡፡

አቶ አሸናፊ አክለውም በቀጣይ በክልሉ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት መነሻ የሚሆን የጋራ ግንዛቤና መግባባት የተደረሰበት መድረክ መሆኑን አንስተው በከፍተኛ ፍጥነትና በጊዜ የለኝም መንፈስ የሚንሰራበትን ሀሳብ የጨበጥንበት ነው ያሉት፡፡

አቶ ሰለሞን ደነቀ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የወሳኝ ኩነት ዘርፍ ኃላፊ፣ በክልሉ በሁሉም ተቋማት ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ፣ አበረታችና በተጨባጭ ለውጥ የታየበት መሆኑን ከቀረበው ከግማሽ ዓመት ሪፖርት መረዳት የተቻለበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በተለይም ከኢኮኖሚ አንፃር በሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በሰፊ እየተነሳ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቀነስ እየተሰሩ ያሉ ምርትና ምርታማነት የማሳደጉ ተግባር የተሻለ መሆኑን ገልጸው በማህበራዊ ዘርፍም በጤናው ዘርፍ በማህበረሰቡ ዘንድ እየተነሰ ያለው የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል ህብረተሰቡን በማስተባበር ሁሉም የመንግሥት እና የፓርቲው አመራር በሰጠው ልዩ ትኩረት ይህንን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል የተካሄደበት አግባብ ተስፋ ሰጪና ውጤታማ ነው ብለዋል፡፡

የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የንፁህ ውሃ መጠጥ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋልታሞ ደብሎ በበኩላቸው ይህ መድረክ ፓርቲው ብልጽግና ሁለተኛ ጉባኤ በስኬት ያጠናቀቀበት ማግስት የሚደረግ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በመሆኑ ልዩ ያደርጋዋል ነው ያሉት፡፡

በሚቀጥሉት ጊዜያት ከህዝቡ፣ ከመሪው ብልጽግና እና ከመንግሥት ጋር በመሆንና ህብረተሰቡን በማስተባበር የህዝብ የልማት ጥያቄን መመለስ እንችላለን ያሉት አቶ ፋልታሞ በክልሉ አጋዥ የሆኑ ምቹ ሁኔታዎች አሉን ለዚህም አመራሩ ቀረብ ብሎ የመሠረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለይቶ መስራት የሚፈልግ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

የክልሉ የመንግሥት ግዥ አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ የሺሃረግ ደበበ የክልሉ አመራር ከታችኛው አመራር ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠርና እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ወርዶ የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ከማጉላት አንፃር ሰፊ ስራዎች ለመስራት መግባባት የተፈጠረበት መድረክ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ት ቤት የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ ሰብለፀጋ አየለ፣ በየተቋማቱ ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ ጠንካራ ጎኖች ባሻገር በአፈፃፀም ሂደቱ የታዩ ውስንነቶችን በቀጣይ ማረምና የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ በሚያስችል መልኩ ምክክር መደረጉ ጠቁመዋል፡፡

በተለይም የመንግሥት ኢንሼቲቪ የሆኑ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በትምህርት እና በጤናና መሰል ጉዳዮችን ለማሳካት ከመድረኩ የተቀመጠውን አቅጣጫ መሠረት በማድረግ ሁሉም የየድርሻውን ወስዶ ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

አስተያየት ሰጪዎቹ በመጨረሻም በክልሉ በ6ወራት በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፍ የተመዘገበው የተሻለ አፈፃፀም በማስቀጠል እና በጉድለት የተገመገሙ ጉዳዮችን በመለየት ከክልል እስከ ታችኛው መዋቅሮች ድረስ ህዝቡን በማስተባበር ትኩረት ሰጥቶ መስራት የሚጠበቅ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *