hhhj

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2017 ዓም የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ከመንግስት የአስፈጻሚ ተቋማት ጋር እየገመገመ ነው።

በግምገማው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ፣ የክልሉ አስተባባሪ አካላት፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳድር አስተባባሪዎች በተገኙበት ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2017 የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸምን ሪፖርት እያቀረቡ ያሉት የፓርቲው የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፍ አቶ ነጋ አበራ በሪፖርቱ እንዳብራሩት በክልሉ ባለፉት ወራት በፓርቲው መሪነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና መሠረት የሚጥሉ በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ና ፖለቲካዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተቀናጀና የተደራጀ ስራዎች በመሰራታቸው

በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ፓርቲው በንቅናቄ ከሚመሩትና የትኩረት አቅጣጫ ከሆኑት ውስጥ አዎንታዊ ሰላምን ማረጋገጥ፣ የተረጅነት አስተሳሰብና ተግባርን በተግል በመምራት መሻገር፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሆኑት የመንግሥት አገልግሎት ለማሳለጥ ትከረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑነ ገልጸዋል።

ጠንካራ የፓርቲው ተቋማዊ አደረጃጀቶችን በመፍጠር በክልሉ ለሚከናወኑት ሁለንተናዊ ልማትን ለማሳለጥ ምቹ ሁኔታ መፈጠር እንደተቻለ የገለጹት አቶ ነጋ በቀጣይ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞን ከዳር ለማድረስ የትኩረት አካል እንደሆነ ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰአት የተግባር አፈጻጸም እየተካሄደ ሲሆን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተብራርቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *