
በታርጫ ከተማ ተደብቀው ለዘመናት ጓዳ የቆዩ እምቅ ሀብቶች በለውጡ መንግሰት ብልጽግና ፓርቲ መሪነት ወደ ሜዳ ወጥተው ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል።
ታርጫ ከተማ በ1993 ዓ.ም የዳውሮ ዞን ዋና ከተማ በመሆን ተመስርታለች። ከተማዋ አንድ ቀበሌ ብቻ ይዛ የተቋቋመች ሲትሆን አሁን 2 የከተማና 5 የገጠር ቀበሌያትን አጠቃላይ 7ቀበሌዎችን ያቀፈች ናት። ከተማዋ ሲትመሰረት ወደ 15ሺ የህዝብ ብዛት የነበረው ሲሆን አሁን ላይ የዳውሮ ዞን ዋና መቀመጫና የታርጫ ከተማ አስተዳደር መቀመጫ ከመሆን ባለፈ የደቡብ ምዕራብ ክልላዊ መንግስት ማህበራዊ ክላስተር መቀመጫና የታርጫ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር መቀመጫም ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ከ75 ሺህ በላይ ህዝቦች እንደሚኖሩባትና የህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነም መረጃዎች ያመላክታሉ።
ታርጫ ከተማ የታርጫ ከተማ አስተዳደር መቀመጫ; የታርጫ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር መቀመጫ; የዳውሮ ዞን ዋና ከተማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ከብዝሃ ዋና ዋና ከተሞች መካከል አንዷ በመሆን ክልሉ የህግ አውጪ ክላስተር መቀመጫነትም እያገለገለች ትገኛለች።
አከባቢው ለከተማም ሆነ ለገጠር ኢንቨስትመንት እምቅ አቅም ይዘው ግን የእምቅ ሀብት ጠባቂ እንጂ ተጠቃሚ ሳይሆን ለበርካታ ዘመናት ከእይታ ውጭ በመሆን ተደብቀው እንደቆና በብልጽግና ፓርቲ መሪነትና በለውጡ መንግስት ጥረት ሀብቶቹ ጥቅም ላይ መዋል መጀመራቸውን ”ቆይታ ከእኛ ጋር ዝግጅት እንግዳችን”የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ወንድሙ ገልጸዋል።
በዛሬው ቆይታ ከእኛ ጋር እንግዳ! ዝግጅታችን አጠቃላይ የታርጫ ከተማ አስተዳደር የስራ እንቅስቃሴን በሚመለከት የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከታርጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ወንድሙ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
”ቆይታ ከእኛ ጋር እንግዳ ዝግጅት”ከከተማ ከንቲባው ጋር የተደረገው አጠቃላይ ቆይታ እንደሚከተለው ቀርበዋል መልካም ንባብ!
መ/ኮ ፦በቅድሚያ ለቃለ ምልልሱ ፍቃደኛ ስለሆኑ እናመሰግናለን
አቶ ዳዊት ወንድሙ፦እኔም ቆይታ ከእኛ ጋር እንግዳችሁ ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ!
መ/ኮ፦ስምና ኃላፊነትዎን ቢገልጹልን?
አቶ ዳዊት ወንድሙ ፦ስሜ አቶ ዳዊት ወንድሙ የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ
መ/ኮ፦የታርጫ ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ የስራ አንቅስቃሴ ምን ይመስላል?

አቶ ዳዊት ወንድሙ ፦ታርጫ ከተማ ከአመሰራረቷ ጀምሮ በፕላን የተመሠረች ከተማ ናት።አንድ ከተማ ለነዋሪዎች ምቹና ፅዱ የሚሆነው እንዲሁም ከተማን ከተማ የሚያስብለው የከተማ መሠረተ ልማት አውታሮች ማሟላት ሲችሉ ሲሆን ታርጫ ከተማም የዚሁ ዕድል ተጠቃሚ እንዲትሆን የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን የመዘርጋት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
የከተማ መሠረተ ልማቶችን ከማሟላት ባሻገር በከተማው በርካታ ቱሪስቶች የሚያቋርጡ በመሆኑ ከተማውን ከቱሪስት መተላለፊያነት ወደ መናገሻነት እንዲትሻገር አስፈላጊ መሠረተ ልማት አውታሮች እንዲዘረጉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትኩረት የሚሰራ ጉዳይ እንደሆነም የከተማ ከንቲባው ይናገራሉ።
የለውጡ መንግስት የኢትዮጵያ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአከባቢውን ገጽታ መጥተው ካዩና ከጎበኙ በኋላ ለአከባቢው በሰጡት ልዩ ትኩረት ከዕይታ ውጭ በመሆን ተደብቆ የቆዩ ሀብቶች ከጓዳ ወደ ሜዳ በመውጣታቸው ሀብቱን ጠብቀው ያቆዩ ህዝቦች የሀብቱ ተቋዳሽ እየሆኑ ይገኛሉ ።
ለአብነትም ኢት ማዕድን ድንጋይ ከሰል ማበልጸጊያ ፋብሪካ በአከባቢው ተሰርተው ስራ በመጀመሩ ለ110 ዜጎች ቋሚና ለ125 ዜጎች ጊዜያዊ በድምሩ 235 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን እና ከፋብሪካውም የአከባቢው መንግስት በወር በአማካይ ከ350 ሺህ እስከ 4መቶ ሺህ ብር የስራ ግብር እያገኘ ይገኛል።
ከተማዋ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ከመንገድ መሠረተ ልማት አኳያ የከተማ እና የከተማ ገጠር ቀበሌያትን ከከተማ ጋር ለማስተሳሰር በመንግሥት፣ በባለሀብቶች ድጋፍና እና በህብረተሰብ ተሳትፎ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታና ጠጠር ማልበስ ብሎም ሌሎች የመንገድ መሠረት ልማት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ።
በማህበራዊ ዘርፍ ”ትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ”ማህበረሰቡን በማስተባበር ትምህርት ቤቶች ጥገና፣ የውስጥ ቁሳቁስ ማሟላት፣ የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥና የተማሪዎች ተሳትፎ ማሳደግ እንዲቻል ታርጫ ከተማ ሶሬ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቅድመ አንደኛ ክፍል የምገባ አገልግሎት እንዲሁም በታርጫ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ሀገር ዓቀፍ መግቢያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች አዳር የጥናት ቦታ በማመቻቸት ለእነዚህም የምገባ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩንም ተናግረዋል።
በጤና ዘርፍም መከላከልን መሠረት ያደረገ ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ የጤና ኤክስቴንሽን፣የቀበሌ አደረጃጀት፣ የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀቶችን; የህዝብና የመንግስት አደረጃጀቶችንና ሌሎች አደረጃጀቶችን ባሳተፈ በተለይም የወባ ወረርሽን መከላከልና መቆጣጠር ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛል። እንዲሁም በጤና ጣቢያዎች የመድኃኒት እጥረት እንዳይገጥም በየጊዜው የመድኃኒት ግዥን በመፈጸም የጤና አገልግሎት አሰጣጥ የማሻሻል ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ከተማ አስተዳደሩ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰላምና ፀጥታ ላይ በሰራው ጠንካራ ቅንጅታዊ ሥራዎች የአከባቢው ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
በከተማ ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ ከተለየው አንዱ በማህበር ተደራጅተው ለመሥራት ስቀርብ የነበረውን ምላሽ ከመስጠት አንጻር ከለውጥ በፊት 120 ነዋሪዎች በ10 ማህበራት ተደራጅቶ የቤት መሥሪያ ቦታ ተጠቃሚ ስሆኑ ከለውጥ በኋላ ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ፓርቲ እንደመሆኑ መጠን ከለውጡ በኋላ 1368 ነዋሪዎች በ99 ማህበር; 220 በክብር የተሰናበቱ ጀግና የመከላከያ ሠራዊት አባላት በ18 ማህበርና 328 መምህራን በ24 ማህበር ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ተጠቃሚ ሆነዋል። ከተማ አስተዳደሩ አሁንም በዚህ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ለዜጎች ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጿል።
በከተማ አስተዳደሩ ከኢኮኖሚ አንጻር በግብርናው ዘርፍ የአከባቢውን እምቅ ሀብት አቀናጅቶ በመጠቀም የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት፣ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር እና በምግብ ራስን በመቻል ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የግብርና ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ሥራዎች እንደተጀመሩም አንስተዋል።
በዚህም የመስኖ ልማት አውታሮችን በመዘርጋት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣በከተማ ግብርና ልማት፣በሌማት ትሩፋት እንሼቲቭ የክልሉ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ሼዶችን በመገንባትና ወጣቶችን በማደራጀት ክላስተር በመመሰረት የዶሮ እና የከብት እርባታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ከፓርቲ ተቀርጾ ለሚወርዱ እንሼቲቮች ትርጉም በመስጠት ህብረተሰቡ እና በየደረጃው ያሉ አመራር አካላትን በማስተባበር የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለመመለስ እየተሰራ ስሆን ለሁሉም ሥራ ሞተር የሚሆነው ገቢ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ወሳኝ ስለሆነ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በታስክ ፎርስ በማቀናጀት የገቢ አሰባሰብ ሥራም በልዩ ትኩረት እየተመራ ይገኛል።
ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ገቢ አሰባሰብ ሥራ ፣የድቺና የእግረኛ መንገድ ግንባታዎች ፣የከተማና ገጠር ቀበሌያት የመንገድ ከፈታና ጠጠር ማልበስ ሥራዎች የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ሲሆኑ ህብረተሰቡ እስካሁን ለከተማው ዕድገት እያደረገ ያለው ሁሉዓቀፍ ትብብርና ድጋፍ በተቀናጀ መንገድ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
በከተማው በርካታ ቱሪስቶች የሚያቋርጡ በመሆኑ ከተማውን ከቱሪስቶች መተላለፊያነት ወደ መናገሻነት ለመቀየር የመዝናኛ ፓርኮች፣የስራ ዕድል ልፈጥሩ የሚችሉ ዘርፎችን ለማስፋት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትኩረት ይሰራል።
አሁንም በፌዴራል መንግስት በኩል በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሚሰራው የከተማው ውስጥ ለውስጥ ቀሪ አስፋልት መንገድ ያለመሠራትና የድቺና የእግረኛ መንገድ ግንባታ ሥራዎች ባለመጠናቀቁ ከህብረተሰቡ ጥያቄ እያስነሳ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጥ ሀሳብ ሰጥተው በከተማው በሁሉም ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል።
የከተማ ከንቲባው ቆይታውን ሲያጠቃልሉ የክልሉ መንግስት ከፈደራል ከሚመለከታቸው ጋር በመገናኘት በአካባቢው በፈደራል መንግስት የተጀመሩ አስፋልት መንገድ ለማስጨረስ ለሚያደርገው ጥረትም አመስግነዋል።
