ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክርቤቱ አባላት ባቀረቡት የ6 ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት በመሠረተ ልማት ዘርፍ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል ፡፡

Spread the love

👉 የአርብቶና ከፊል አርብቶ አደር ልጆችን በሆስቴሎች 179 ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ መሆናቸው

👉 በአርብቶ አደር አካባቢ የሚታየውን የተማረ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ በመጀመሪያ ዲግሪ 116 እና በዲፕሎማ 42 ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑ

👉በአነስተኛ የመጠጥ ውሃ ስራዎች የምንጭ ግንባታ ቤሮ ወረዳ ሲሪት ቀበሌ፣ ሜ/ሻሻ ወረዳ ቂራ ቀበሌ፣ ሜ/ሻሻ ወረዳ ጎሪነሱ ቀበሌ፣ ሜ/ሻሻ ወረዳ ቦኡት ቀበሌ 100% የተጠናቀቁ መሆናቸው

👉 የመንገድ መሠረተ ልማት ሽፋን ለማሳደግ 18 ኪ/ሜ ከባቹማ እስከ ጨበራ DC-2 የጠጠር መንገድ ግንባታ በማጠናቀቅ አገልገሎት እንዲሰጥ ተደርጓል

👉 44 ኪሎ ሜትር ከሀዱባ-ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሶስት መንገድ ከፈታ ሥራ 50% ማድረስ መቻሉ፡፡

👉 20 ኪሎሜትር ቱልጊ- ካሪ -ሞጋ DC-2፣ 31 ኪሎሜትር ከኡፊት ጋራሙጂ DC-2 እና 30 ኪሎሜትር ከጨበራ ያርጣ DC-2 የጠጠር መንገድ ግንባታ የጨረታ ዶክመንት ዝግጅት ተፈጽሟል

👉 የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ 45 ኪሎሜትር ከአደይ አበባ ፎልጁ፣ 60 ኪሎሜትር ከኩምባ -ኦሽካ ዲንቻ-ኮንታ፣ 52 ኪሎሜትር ሞጋ -ናምሪ፣ 50 ኪሎሜትር ጎሪ ጌሻ-ጨለማ ሸጥ መንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ተጀምሯል

👉 ድልድይ ጥናትና ዲዛይን ስራ 5 ድልድይ (ማሙሩ፣ ዴካ፣ ሾሻሮ፣ ሹሪ እና ኩጃጉዱ) 85% መድረሱ

👉 በአርብቶ አደሩ አካባቢ የመስኖ ልማት ከ 150 ሄ/ር የሚያለማ የኪሉ አነስተኛ መስኖ ግንባታ 78% መድረሱ

👉በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ስራዎች በመሬት ልማትና ማኔጅመንት በክልሉ በሚገኙ ከተሞች 377.64 ሄ/ር የለማ መሬት መዘጋጀት መቻሉ

👉 2,039 ሰነድ አልባ ይዞታዎች ሰነድ እንዲያገኙ ተደርጓል

👉 በከተሞች መሠረተ-ልማት ግንባታ ነዋሪዎች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ህብ/ሰቡ 59,889,110 ብር የሚገመት የገንዘብ፣የጉልበትና የቁሳቁስ አስተዋጽኦ ማበርከት መቻላቸው

👉 የክልሉን ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ስራዎች በከተማና በገጠር ክልላዊ የዉሃ ሽፋን ከነበረበት ወደ 43.73% ማድረስ መቻሉ፡

👉 በማዕድን ሃብት ልማት ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚውሉ 50,406 ቶን የድንጋይ ከሰል ማምረት መቻሉ፡፡

👉 የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ በባህላዊ እና በልዩ አነስተኛ ወርቅ አምራቾች ምርትና ግብይት ዙሪያ በተካሄደው እንቅስቃሴ 75.525 ኪ.ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ መቻሉ፡፡

👉 የመስኖ አውታሮች ግንባታ ሽፋንን ከ3641 ሄ/ር ወደ 3856.5 ሄ/ር ለማሳደግ በዘላቂ ልማት ግቦች ማሳኪያ ፕሮግራም 5 ነባር መስኖ ፕሮጀክቶች እና 1 አዲስ ጥገና ( ዳማ፤ ኦልሙ፤ ፅልቤ፤ ውኒ ፤ ሻታ እና ሸዉ ጥገና ) እየተሰሩ መሆኑ

👉 በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም 1077 ሄ/ር መሬት ማልማት የሚያስችሉና 1333 አ/አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የ10 አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሥራን በማከናወን በአማካይ ከነበረበት 34.9% ወደ 43.3% ማድረስ መቻሉ

👉 የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በክልሉ በጀት እየተገነቡ ያሉ 3 መናኸሪያዎች ፊዚካል አፈጻጸም የቦንጋ መናኸሪያ 60% ፣ የሚዛን መናኸያ 72% እንዲሁም የታርጫ መናኃሪያ 83% ማድረስ ተችሏል፡፡

👉 በሁሉ አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ ግንባታ የድልድይ እና መንገድ ግንባታ አቅርቦትን ለማሳደግ የሚገነቡ የድልድይ እና መንገድ ፕሮጀክቶችን የመምረጥና ቀሪ ሥራዎችን የመለየት ሥራ መከናወኑ

👉 በግማሽ ዓመቱ ለግንባታና ጥገና ስራ ከህብረተሰብ ተሳትፎ 116,995,380 ብር መሰብሰብ መቻሉ፡፡

👉 በመንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም- በሚዛን ዲስትሪክት 38.6 ኪ.ሜ ፣ በታርጫ ዲስትሪክት 12 ኪ.ሜ ፣ በቦንጋ ዲስትሪክት 24 ኪ.ሜ መገንባቱን ርዕሰ መስተዳድሩ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *