

የትምህርት ለትውልድ ኢንሼትቭ ስራዎችን ውጤታማ ለማደረግ በጥሬ ገንዘብ፣ በአይነት እና በጉልበት 142,146,033 ብር ተሰብስቧል፡፡
የቱልጊት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉና በክልሉ መንግስት ድጋፍ እየተገነባ ሲሆን ግንባታዉ ከ 90% በላይ ማድረስ ተችሏል፡፡
የትምህርት ተሳትፎ ከቅድመ አንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል 734,496 ተማሪዎች በመማር ላይ መሆናቸው፡፡
የአንደኛ ደረጃ መማሪያ መጽሐፍ በህብረተሰብ ተሳትፎ ብር 161,205,719 እና ከመንግስት 60,000,000 ብር በድምሩ 221,205,719 ብር ተሰብስቦ 1,023,837 መጽሐፍ በማሳተም ተሰራጭቷል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የስታንዳርድ ኦዲት በማከናወን ከስታንደርድ በታች የሆኑ 11 የግል ኮሌጆች የተዘጉ ሲሆኑ 9 ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ቴክኒክና ሙያ ስልጠና የገቡ ሰልጣኞች በመደበኛ ነባር ሰልጣኞች 5856 ፣ አዲስ ሰልጣኞች 4480 ተከናዉኗል፡፡
የውጪ አገር ስራ ስምሪትና ስልጠና ለ 3179 ዜጎች ተከናዉኗል፡፡
የስራ ዕድል ፈጠራ በቋሚ 18,200 በጊዜያዊ 81,738 በድምሩ 99,938 መፍጠር ተችሏል።
ውጭ ሀገር ሄደው ለመስራት የሚፈልጉ 209 ዜጎች ከኢምግሬሽንና የዉጭ አገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የስራ ዕድል እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
የወባ በሽታ መከ/መቆጣጠርን በተመለከተ ምርመራ ከተደረገላቸው 1,179,849 ሰዎች ውስጥ 750,489 ሰዎች የወባ ተዋሲያን በደማቸው የተገኘባቸው ሲሆን የወባ የመገኘት ምጣኔ 63.6% ደርሷል፡፡
ኤች አይ ቪን ለመከላከልና ለመቆጣጠር 90,348 ምርመራ የተከናወነ ሲሆን 580 ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ተገኝቷል፡፡
በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች 30,721 እናቶች የወሊድ አገልግሎት አግኝተዋል፡፡
የደም ባንክ አገልግሎት 1193 ዩኒት ደም ተሰብስቧል፡፡
የጤና ተቋም መሰረተ ልማት ግንባታዎችን የማስጨረስና ለረዢም ጊዜ ግንባታቸዉ የቆሙትን ዉለታ በማቋረጥ በክልሉ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዉል በመግባት እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡
የሴቶችን የሥራ ጫና ለማቃለል 29,960 ሴቶች ዘመናዊ የሆኑ ጊዜ እና ጉልበት ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ ሆነዋል ፡፡
644,558 በክረምት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳትፈዋል።
2,619,560 የህብረተሰብ ክፍሎች በወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡
የተከናወኑ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራት በገንዘብ ሲተመን 604,422,460 መፈጸም ተችሏል፡፡
በ 11 የቅርስ የስብስብ ማዕከላት 1472 ቅርሶች ተሰብስበዋል፡፡
በቱሪዝም ዘርፍ የሥራ ዕድል በቋሚ 427 በጊዜያዊ 2501 ተከናዉኗል፡፡
ልዩ ልዩ ሀገር በቀል ዕውቀቶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁና እንዲለሙ ተደርጓል
የህዝብ ለህዝብ ትስስር በሚያጠናክሩ ኩነቶች የዘመን መለወጫ ክብረ- በዓላት በጋራ ተከብሯል፡፡
በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ዉድድር በማካሄድ 8,914 ስፖርተኞችንና አትሌቶችን ማሳተፍ መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አቅርበዋል።
በታጠቅ አበበ
