ቱባ ባህልን ጠብቆ ያቆዩት አባቶች ልመሰገኑ ይገባል፦ የበዓሉ ተሳታፊዎች

Spread the love

የ2016 ዓ/ም የካፈቾ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል /የቤነ ሻዴዬ ባሮ/ በቦንጌ ሻምበቶ በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በዓሉ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በንጉሡ ምርቃት ተከፍቶ የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ የእርቅና የምርቃት ስነስርዓት በማከናወን ተከብሯል።

በዝግጅቱ የተለያዩ ባህላዊ የሙዝቃ ትርዒቶች ከሁሉም የዞኑ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር በመጡት ባህላዊ ሙዝቃ ተጫዋቾች ቀርቧል።

የቀደምት ካፈቾ ህዝብ በንጉሡ የሚመራ ምክረቾ (የአስተዳደር የምክር ቤት) የነበረው በመሆኑ የቆየና ለሀገር ሠላምና ደህነት ፋይዳ ያለው የዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ልምድ ባለቤት መሆኑን የገለጹት የካፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ይህ የምክር ቤት አስተዳደር ስረዓት በጎሳና በሀይማኖት ላይ ያልተመሠረተ የአመራር ጥበብን መሠረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዓሉን በጋራ ማክበሩ የህዝብ ለህዝብ ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ክልላዊ አንድነትን ለማጽናት የጎላ ሚና እንዳለው የገለጹት የበዓሉ ተሳታፊዎች ወጣቱ ትውልድ የጥንት አባቶቹን ታሪክና ባህል የማልማትና የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል።

ቀደምት የካፋ ነገስታት ታሪክን ጠብቆ ያቆዩ አባቶች ልመሰገኑ ይገባል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በበዓሉ ላይ በመታደማቸው ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

በበዓሉ ማጠናቀቂያ ላይ ተጋባዥ እንግዶች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *