

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን የማንነት መገለጫ ለማዘጋጀት የሚያስችል የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈረመ፡፡
ስምምነቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘዉ ተሻገር፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ስምምነቱን ፈርመዋል።
ስምምነቱ የኢቲኖግራፊና የቋንቋ ባህሪያትን ለማሰናዳት ያስችላል ተብሏል፡፡
አፈ ጉባኤ አገኘዉ ተሻገር፤ ስምምነቱ የብዝኃ ልሳንና ብዝኃ ባህል ባለቤት የሆነችዉን ኢትዮጵያን በውል ለማወቅ የሚያስችል የማንነት ዝግጅት መሆኑን ነዉ ያስረዱት፡፡
የብሔረሰቦች የማንነት መገለጫ ዝግጅት ሥራ ለአምስት ዓመታት የሚከናወን ይሆናል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡
