



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አክልሉ ለማ የዛሬው ትውልድ ዳግም አድዋን በመድገም በኢኮኖሚ አሸናፊነት እና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ያጠናከረ ዜጋ በማፍራትና ከተሞች ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑበ ማድረግ ዘወትር በየሣምንቱ የፅዳት ዘመቻ ማድረግንእንደምገባም አሳስበዋል ።
የታርጫ ከተማ ከንቲባ አቶ ዳዊት ወንድሙ በበኩላቸው ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ የተጀመረው የጽዳት ዘመቻ በየሣምንቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና አባቶቻችን በአድዋ በወራሪው ኃይል የተቀዳጁትን ድል የዛሬው ትውልድ በኮርደር ልማት እንድሁም በሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ አለብን ስሉ ገልጸዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አህመዲን አወል የአድዋ በዓል መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በከተማው መደረጉ የሚበረታታ ተግባር ነው በማለት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማዘዋወር ከተለያዩ በሽታዎች ራሰን በመከላከልና ጤናማ ዜጋ መሆን እንደሚገባ ገልጸዋል ።
በመርሀ-ግብሩ የከተማው የህብረተሰብ ክፍሎች የክልል፣ የዳውሮ ዞን፣ የታርጫ ዙሪያ ወረዳ እና የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች እና ስፖርተኞች የተገኙት ሲሆን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል።
