




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የልማት አቅምና ጸጋ መነሻ በማድረግ በተዘጋጀዉ የቀጣይ ሶስት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተጀምሯል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) የክልሉ የቀጣይ ሦስት ዓመታት ዕቅዶች ከመደበኛው የአሠራር ስርዓት ለየት ባለ መንገድ ተፈጥሮአዊና ሰብአዊ ሀብቶቻችን ተጠቅመን ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚ ለመቀየር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የክልሉ የቀጣይ ሦስት ዓመታት የልማት አቅምና ጸጋ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀዉን ዕቅድ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በማውረድ እምርታዊ የሆነ ለውጥ ለማምጣት የድጋፍና ክትትል አግባቡ ውጤትን መሠረት ባደረገ መልኩ መሠራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ የልማት አቅምና ጸጋ መነሻ በማድረግ የተከለሰ የክልሉ የተለያዩ ዘርፎች የቀጣይ ሶስት ዓመት ዕቅድ ሰነድ እየቀረበ ሲሆን በቀረቡት ሰነዶች ላይ ውይይት የሚደረግና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ይጠበቃል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
