የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አዲስ አበባን “እየፈካች ያለች የአፍሪካ ከተማ” ሲሉ ገልፀዋታል

Spread the love

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት በጆሀንስበርግ ከተማ ባደረጉት ንግግር ላይ በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከተማዋን እጅግ ውብ፣ ፅዱ እና ለኢንቨስትመንት ምቹ እንድትሆን አድርጓታል ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደውን እና የጆሀንስበርግ ከተማ የምታስተናግደውን የጂ 20 የመሪዎች ስብሰባን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ላይ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ ከ10 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን እንደተረዱ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ነዋሪዎች በቀን ብቻ ሳይሆን በምሽትም ጭምር ያለምንም ችግር በምቹ ጎዳናዎች ላይ እንደልባቸው መንቀሳቀስ የሚችሉባት ሰላማዊ፣ በመንገድ ዳር ውብ መብራቶች ያሸበረቀች እና የፈካች ከተማ ሆናለች ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ራማፎሳ በቅርቡ ለአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ በተገኙበት ወቅት በከተማዋ በምሽት ሲዘዋወሩ ከተማዋ ውብና ንፁህ በመሆኗ ፍቅረኛሞች በምቹ ጎዳናዎች ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲዝናኑ መመልከት እንደቻሉም ነው የተናገሩት።

የከተማዋን ገፅታ የቀየረው የኮሪደር ልማት ለጆሀንስበርግ ከተማ ምርጥ ተሞክሮ በመሆኑ ትምህርት መውሰድና ከተማዋን መልሶ በማልማት ለጂ20 የመሪዎች ጉባኤ ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባም ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *