






የሸካ ዞን ጤና መምሪያ የተገልጋዮች ቅሬታ እውነት መሆኑን አጣርቼ ለእርምት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ቅየህብረተሰብ ክፍሎችና ታካሚዎች እንደገለጹት ታክሞ ለመዳን እየመጣን በመፀዳጃ ቤት ጉድለት ላላስፈላጊ በሽታ እየተዳረጉ መሆኑን ገልጸዉ የባለሙያ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣የአልጋ ና የመድሀንት እጥረት እንዳለ ገልጸዋል።
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጂ አቶ ተገኝ ገቦ በበኩላቸው ሆስፒታሉ ከ2010 ዓ .ም ወዲህ ከመጀመሪያ ደረጃ ወደ አጠቃላይ ሆስፒታል ማደጉን ተናግረዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የታካሚው ቁጥር በመጨመሩ ምክንያት ታካሚዎች ላይ የህክምና እጥረት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር እያጋጠመ መሆኑንም ገልጸዋል።
የቴፒ አጠቃላይ ሆሲፒታል ሚዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር እንዳለው አባይ ከተገልጋዩ የተነሳው ቅሬታ ተገቢ መሆኑን ተናግረው ይህም የሆሲፒታሉ የገቢ አቅም በማነሱ ነው ብለዋል።
የሸካ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ እምሩ ወየሳ በሆስፒታሉ ላይ የተነሳው ቅረታ ተገቢ መሆኑን በመግለፅ ችግሩን ለመፍታት ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በቀጣይ ሆሲፒታሉ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የቦርድ አባላት የተለያዩ ውሳኔዎችን ከማስተላለፍ ጀምሮ ምቹ ሁነታ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑንም መጥቀሳቸዉን ማሻ ኤፍ ኤም ዘግቧል።
