ህብረብሄራዊ አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት የሀገረ መንግስት ግንባታና የመንግስታት ግንኝኑነት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ በሚል መሪ ሀሳብ ለክልልና ለዞን ባለድርሻ አካላት ጋር በሚዛን አማን ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግገር ያደረጉት የክልሌሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ

የተከበሩ አቶ መቱ አኩ በክልሉ ለሚደረገው ሀገረ መንግስት ግንባታ የሰላም ግንባታን ማጽናት ዋንኛ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው ሀገረ መንግስት ግንባታን ከብሄረ መንግስት ግንባታ ጋር አጣምሮ ለመሄድ ነጠላ ትርክቶችን በማስቀረት ገዢ ትርክቶች እንዲሰርጹ ለማስቻል ባለድርሻ አካላት ሀገር በቀል ዕውቀትን ከዘመናዊ ህጎች ጋር በማጣመር ግጭቶችን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት በሚያስችል መልኩ መስራት አለባቸው ብለዋል ።

አክለውም በስልጠና የታደሙ ባለድርሻ አካለት ለሰላም ያላቸውን አዎንታዊ ሚና በመገንዘብ ትኩረት ሰጥተው እንዲደግፉ አሳስበዋል።

በዉቢት ደበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *