የኮንታ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ።

Spread the love

የኮንታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ የስራ ዘመን 23ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ የጀመረ ሲሆን በጉባኤው የምክር ቤቱ የ2017 ዓ/ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የአስፈፃሚዎች የ2017 ዓ/ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2017 ዓ/ም የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ እንደሚፀድቅ ተገልጿል።

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለ2 ቀናት ቆይታ ሲያደርግ ሌሎችም በዞን መንግስት የተገዙ የግንባታ ማሽን መተዳደሪያ ሞሽን፣ በ2016 ዓ/ም የተሰበሰበ ትርፍ ገቢ ረቂቅ በጀት እና የተለያዩ ሹመቶች ቀርበው እንደሚፀድቁም ይጠበቃል።

የዞኑ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ብርሃኑ አቱሞ በጉባኤው መክፈቻ ንግግራቸው ም/ቤቱ ከፍተኛ የፖለቲካ ስልጣን ባለቤትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ዋነኛ ተቋም መሆኑን ገልፀው ይህንንም ኃላፊነት ለመወጣት እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በዞኑ በቀጣይ የቀበሌ ም/ቤቶች ጉባኤ ማጠናከር፣ የኦዲት ግኝት ዕዳ አመላለስ ማጠናከርና መሠል ጉዳዮች በትኩረት የሚከናወኑ መሆናቸውን የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *