



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ ከስድስት ዞኖች፣ከተመረጡ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ እንደገለጹት፣የክልሉን የፋይናንስ አሰራር ስርዓቱን እስከ ታችኛው መዋቅር ወጥ በሆነ መልኩ በመዘርጋት የድጋፍ እና ክትትል ስራዎችን በማጠናከር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አክለውም ወጥ የሆነ የፋይናንስ ሪፖርት ስርአት ለማዘመን ፣ጠንካራ የበጀት አጠቃቀም ስርዓት ለመዘርጋት ፣እንዲሁም ውስን የሆነውን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም የፋይናንስ ስርዓቱን ለማጠናከር መወያየት እና የጋራ ግንዛቤ መያዝ ተገቢ እንደሆነም ገልጸዋል ።
በተለይ የኦዲት አመላለስ ሂደት፣በንብረት አያያዝና አጠቃቀም እንዲሁም ከገቢ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስተካከል እንዲቻል በዘርፋ ለሚገኙ አካላት የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ ጠቁመዋል።
በውይይት መድረኩ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ለስድስት ዞኖች፣ለተመረጡ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በመስክ ምልከታ ወቅት የተገመገመ የመስክ ምልከታ ግብረ መልስ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
