የክልሉ ግቢርና ቢሮ ሆርቲ ካልቸር ልማት በአቮካዶ ማጋባት/ Grafting/ ዙሪያ ለዞንና ለወረዳ ግብርና ባለሙያዎች ስሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ በእርሻና ሆርቲ ካልቸር ልማት በአቮካዶ ማጋባት/ Grafting/ ዙሪያ ለዞንና ወረዳ ግብርና ባለሙያዎችና ለችግኝ ጣቢያ አስተባባሪዎች በቴፒ ከተማ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ስሰጥ የነበረዉ የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል።

ስልጠናዉ በአቮካዶ ማጋባት/ Grafting/፣ የፓፓያ ተክል አመራረትና በሆርቲካልቸር ሰብል ላይ የሚከሰቱ ተባዮች ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ገለፃ የተደረገበት ስሆን በዛሬዉ ዕለት በቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል ላይ የአትክልትና ፍራፍሬ ዘር አዘገጃጀትና አዘራር፣አትክልት አተካከል፣የፍራፍሬ ችግኝ አደቃቀል (ግራፍቲንግ) ማድረግ ፣የፍራፍሬ ተክል አገራረዝ ዘዴ ላይ የተግባር ስልጠና ልምምድ አድርገዋል፡፡

በተግባር የተደገፈ ስልጠና በግብርናዉ ዘርፍ የተሻለ ዉጤት ለማምጣት እንደሚረዳ የተገለጸ ሲሆን በተግባር ስልጠናዉ የተለያዩ የአቦካዶ ዝሪያዎችን በማዳቀል የተሻለ ምርት ማግኘት እንደሚቻልና የፓፓያ ዘር በፖሊ እንዴት እንደሚዘጋጅ በሰፊዉ መመልከት ተችሏል።

ስልጠናዉ አዳድስ ነገሮችን ያወቅንበትና የረሳናቸዉን ነገሮች ማስታወስ የቻልንበት ነዉ ያሉት ስልጠናዉን ስወሰዱ የነበሩ የፍራፍሬ ልማት ባለሙያዎች በፅንሰ ሀሳብና በተግባር በወሰዱት ስልጠና ያገኙትን ክህሎት ስራ ላይ እንደሚያዉሉት ገልጸዋል።

በሆርቲ ካልቸር ልማት ዘርፍ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ በቴክኖሎጂ በመታገዝ በብዛት መስራት እንደሚያስፈልግ አንስተው የድጋፍና ክትትል ሥራውን አጠናክሮ እንደሚያስቀጥሉም ተናግረዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ በእርሻና ሆርቲ ካልቸር ልማት ዘርፍ የፍራፍሬ ልማት ባለሙያ አቶ ምትኩ መንገሻ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዘዴዎችን በመጠቀም ምርትን በብዛትና በጥራት በማምረት ለአርሶ አደሩ ብሎም ለሀገር ኢኮኖሚ የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት ታስቦ የተሰጠ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ስልጠና መሆኑን አብራርተዋል ።

በክልሉ በ201 በጀት ዓመት 450 ሺህ የፍራፍሬ ችግኞችን ግራፍቲንግ ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ምትኩ የግብርና ባለሙያዎች የሆርቲ ካልቸር ልማት ዘርፍ ምርታማነት ለማሳደግ በቴክኖሎጂ በመታገዝና የተሻሻሉ የአሠራር ዘዴዎችን በመጠቀም ለአርሶ አደሩ ያልተቋረጠ የክትትልና የኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በንድፈ-ሀሳብ የተደገፈ የክህሎት ስልጠና መሰጠቱ የባለሙያውንና የአምራች አርሶ አደሩን የግንዛቤና ክህሎት ክፍተቶች በመሙላት ከፍራፍሬ ልማት በላቀ ደረጃ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ጠቁመው በአቮካዶ ተክል ላይ የተጀመረው ኢንሸቲቭ ተጠናክሮ አንደሚቀጥል ተናግረዋል።

አቶ ምትኩ አክለውም ያሉንን ከፍተኛ የፍራፍሬ ሽፋን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ወደ ምርት ለመቀየር ከግብራና ዘርፉ በርካታ ስራ እንደሚጠበቅ ገልፀዉ ባለሙያዉ የወሰደውን ስልጠና መነሻ በማድረግ አቅሙን አሟጦ ከተጠቀመ በዘርፉ ትልቅ ለዉጥ ማስመዝገብ እንደሚቻል ገልጸዋል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *