



በዚህም በዳዉሮ ዞን ከጪ ወረዳ በከጪ ቱታ ቀበሌ ገበሬዎች ማሠልጠኛ እና በወጣቶች የለማዉ የካሮት ምርት ለተጠቃሚዎች በቅናሽ ዋጋ መቅረቡ ተገልጿል።
ይህ ተግባርም የአካባቢዉ ህብረተሰብ ፍላጎትን ለማርካት እና በተለያዩ አማራጮች የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት በተቋማት እና በአደረጃጀት ደረጃ ማምረት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ስለመሆኑ ማሳያ ነዉ ተብሏል።
በወረዳዉ በተቋማት የተመረቱ ጓሮ አትክልቶች ለተጠቃሚዎች በተመጣጠነ ዋጋ በተለያዩ ጊዜ ስቀርቡ ቆይተዋል፣ አሁን ላይም እየቀረበ ይገኛል።
ከነዚህም በኃይማኖት፣ በመንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ባልሆነ፣ በFTC፣ ትምህርት ቤቶች እና በመሳሰሉት ተቋማት የጓሮ አትክልቶችንም ሆነ ሌሎች ምርቶችን ማምረት ያለዉ ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል።
ከገበያ ከሚሸምቱ ዋጋ እና መጠን በተሻለ ሁኔታ ማግኘት መቻላቸዉን የተናግሩት ተጠቃሚዎቹ የተጀመረዉ መልካም ተግባር ቀጣይነት እንዲኖረዉም ጠይቀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የተመረተዉን ምርት ህብረተሰቡ ከማሳዉ እንዲሸምቱ ክፍት መደረጉ የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን ታሳቢ ያደረገ ነዉ ብለዋል።
በቀጣይም እየደረሰ ያሉ የጥቅል ጎመን፣ የቀይ ሥር፣ የቡና ችግኝ እና መሰል የተቋሙ ምርትን ለህብረተሰብ ክፍት እንዲያደርጉ አሳስበዉ በስፋት እንዲያመርቱም አስተያየት ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ተጠቃሚዎቹ ይህ በሌሎች በወረዳዉ አከባቢዎችና ተቋማት መስፋት ይገባልም ማለታቸዉን
የዘገበዉ የከጪ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።
