




በቦንጋ ከተማ ሁለተኛ ሳምንት የእሁድ ገበያ (Sunday market) መጠኑንና ዓይነቱን ጨምሮ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በባለፈው ሳምንት የዞን እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር መከናወኑን ያስታወሱት የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ንግድ እና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወዳጆ ደሳለኝ ሁለተኛ ሳምንት የእሁድ ገበያ (Sunday market) መጠኑና ዓይነቱን ጨምሮ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
አሁናዊ ያልተገባ የኑሮ ውድነትን በማስተካከል ማህበረሰብን በተመጣጣኝ ዋጋ: በዓይነት ፣ በመጠን እና በጥራት የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ ተግባሩ በቋሚነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።
በእሁድ ገበያ ከግብርና ምርት እስከ ፋብሪካ ምርት የማቅረብ ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ወዳጆ ሸማቹ ማህበረሰብ የሚፈልገውን ምርት መንግስት እና ፓርቲ ለህብረተሰቡ ጥቅም ቅድሚያ ሰጥተው ካዘጋጀው ቦታ በመሸመት እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል የዘገበው የቦንጋ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ነው።
