በፋይናንስ አሰራር ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመፍታት ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች፣ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ ኦዲተሮች በኦዲት መሠረታዊ ፅንስ ሀሳብ ፣ኢንስፔክሽንና የውስጥ ኦዲት አፈጻጸም እንዲሁም የሂሳብ አያያዝና አስተዳደር ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።

የክልሉ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ የሺሀረግ ደበበ በስልጠናዉ መክፈቻ ላይ እንዳሉት፣ የኦዲት ስራ በቂ ዕውቀት ፣ክህሎት እና ልምድ መያዝን የሚፈልግ በመሆኑ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸው በቀጣይ የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡም መልዕክት አስተላልፈዋል።

አክለውም፣የውስጥ ኦዲት ለመንግሥት መስሪያ ቤት ተጨማሪ እሴት የሚፈጥር እና በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሠረተ ማረጋገጫ እና የምክር አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ የተቋቋመ መሆኑን ጠቅሰው ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ደንብ እና መመሪያዎችን ጠንቅቆ ማወቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አያይዘውም፣በፋይናንስ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የፋይናንስ ባለሙያዎች እና ኦዲተሮች በመመሪያዎችና ደንቦች ላይ የተቀመጠውን የአሰራር ደንብ ተከትለው መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በክልሉ ኢንስፔክሽን የውስጥ ኦዲት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አማኑኤል ጀበሮ

በኢንስፔክሽን፣የውስጥ ኦዲት አፈፃፀምና ሙያዊ ስነምግባር መመሪያ ላይ ስልጠና በሰጡት ወቅት እንደገለፁት፣ የሙያ ስነምግባር መርሆዎችን መከተል የኦዲት ተግባራትን ለማከናወን እና በኦዲት ስራው በራስ መተማመን የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል።

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *