


በክልሉ ያሉትን ፀጋዎች በተገቢው በማልማት ከተረጂነት ለመላቀቅ የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ መረባረብ ያስፈልጋል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ
ከተረጂነት መላቀቅና የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ በሚል መሪ ሀሳብ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄ ይገኛል ።
በውይይቱ መድረክ የክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንደተናገሩት በክልሉ ያሉትን ሀብትና ፀጋዎችን በመፍጠርና በመፍጠን እሳቤ በተሰማራንበት የሥራ ዘርፍ ሁሉ ከተረጂነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት ርብርብ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በቀጣይ ውጤታማ የህዝቡ ንቅናቄ በመፍጠር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በማሳደግ ገበያውን ለማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ለማቅለል፣ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ የተጀመሩ ጥረቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ሥራ አጥነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።
ከተረጂነት ለመላቀቅ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን በተግባር ሂደት የተስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ በስፋትና በጥራት በማምረትና ሻጭና ሸማችን በማስተሳስር የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል ጠንካራ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።
