ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል:-

Spread the love

👉 ባለፉት ስምንት ወራት በዋና ዋና የኢኮኖሚ አመላካቾች ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል፣

👉 በቀጣይ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ይህን ስኬት ማጠናከር ከተቻለ ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ8 ነጥብ 4 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች፣

👉ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች ቢያጋጥሙም ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባች፣

👉 በዘንድሮው ዓመት ብቻ በአነስተኛ አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን ከ17 ነጥብ 3 ወደ 20 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር ማደግ ችሏል፣

👉 በኩታ ገጠም እንቅስቃሴ እስከባለፈው ዓመት 8 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት የተሸፈነ ሲሆን÷ ዘንድሮ ወደ 11 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር ማደግ ችሏል‹

👉 በመኸር ወቅት እርሻ ብቻ 4 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት በስንዴ ተሸፍኗል፣

👉 በድምሩ በዚህ ዓመት ከ7 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር ያላነሰ በስንዴ ሰብል ተሸፍኗል፤ከዚህም ከ300 ሚሊየን ኩንታል ያላነሰ ምርት ይጠበቃል፣

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *