የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከኮንታ ዞን የፊት አመራሮች ጋር በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራት ዙሪያ ምክክር አድርጓል።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በኮንታ ዞን በኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ሥራዎች ምልከታና ግምገማ አድርጓል።

የድጋፍና ክትትል ቡድኑ የዞን ማዕከል፣ የኤላ ሀንቻኖ እና የጪዳ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ስራዎችን ተመልክቶ ግብረ መልስ ሰጥቷል።

የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ጎበና በተቋሙ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን መነሻ ሪፖርት አቅርበዋል ።

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የሚያደርገው ድጋፍና ክትትል የተጀመሩ መልካም ጅማሮዎችን ለማስቀጠልና ጉድለቶችን አርሞ ለመሄድ ያግዛል ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ኢዮብ በዞኑ እየተሰሩ ያሉ የኮሙኒኬሽን ስራዎች አበረታች መሆናቸውን አንስተው ከደራሽ ስራዎች በተጨማሪ ዓላማ ተኮር ኮሙኒኬሽን ስራዎች ላይ በማተኮር ህዝብን የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች ላይ በበለጠ ትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

አያይዘውም ጽ/ቤቱ በክልል ብሎም በሀገር ደረጃ ምርጥ ተሞክሮም ጭምር ቀምሮ ማቅረብ የቻለና በተግባራት አፈፃፀም የተሻለ በመሆኑ በሌሎች ተግባራት ላይም ጥንካሬዎቹን በማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም እንዲሁም ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር ለተሻለ ስኬት መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።

በወረዳዎችና ከተማ አስደተዳደር የሚዲያ አማራጮችን አሟጦ ከመጠቀም ፣ተግባራትን በዕቅድ ከመምራት አንፃር የታዩ ክፍተቶችን ለማረም የታችኛውን መዋቅር ከመደገፍ እና ከማብቃት አንፃር ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አፅንኦት ተሰጥቷል።

የድጋፍና ክትትል ቡድኑ ከዞኑ አጠቃላይ አስፈፃሚ አካላት ጋርም በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራት ዙሪያ ምክክር አድርጓል።

በመድረኩ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ሥራን ውጤታማ ማድረግ ለሌሎች ተግባራት ስኬት የጎላ ሚና እንዳለው የገለፁት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ተቋሙን በመደገፍና በማዘመን ጠንካራ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ተግባራትን በማከናወን በመንግስትና በህብረተሰቡ መካከል ያለውን ተግባቦት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል።

በዞኑ ውስጥ ለኮሙኒኬሽን ተግባራት ምቹ ሁኔታ መፍጠርና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት እንደሚያሻም መገለጹን የዘገበዉ የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *