የሻይ ልማት ከኢኮኖሚ ጠቃሜታው ባሻገር የአካባቢውን ስህነ ምዳር በመጠበቅ ረገድም ሚናው የጎላ ነው፦ አቶ ማስረሻ በላቸው

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን በሻይ አመራረት ዘዴ ላይ ለዞን፣ ለወረዳና ለቀበሌ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል፡፡

የስልጠናውን መድረክ ያስጀመሩት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የሻይ ልማት በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረገው ሂደት ውስጥ ለአካባቢያችን ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት አይናተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የሻይ ልማት ከኢኮኖሚ ጠቃሜታው ባሻገር የአካባቢውን ስህነ ምዳር በመጠበቅ ረገድም ሚናው የጎላ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በክልሉ 2300 ሄክታር መሬት በሻይ ልማት የተሸፈነ መሆኑንና ከዚህም ውስጥ 463 ሄክታር በአርሶ አደሮች የሚለማ መሆኑን እንዲሁም 6500 ቶን የሻይ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ መቻሉን አቶ ማስረሻ ጠቁመዋል፡፡

ለሻይ ልማት ምቹ ስነ ምህዳር ያለውና አርሶ አደሩ በሻይ ልማት ልምድ ያለው በመሆኑ በክልሉ ባሉት ወደተለያዩ ዞኖች ማስፋፋት ላይ ትኩረት ማድረግ ይጠበቃል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ

የክልሉ የሻይ ሽፋን አሁን ከነበረበት 2300 ሄክታር በ2020 ወደ 10475 ሄክታር ለማድረስ ዕቅድ መያዙንና አርሶ አደሮችን በማሳተፍና አልም ባለሀብቶችን በመጋበዝ ከሻይ የሚገኘውን ገቢ ከፍ ለማድረግ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ለዚህም ሰልጣኞች ይህንን የሚሰጠውን ስልጠና በተገቢው በመከተተልና ወደ መሬት በማውረድ በሻይ ልማት ዘርፍ የሚሰራውን ስራ ውጤታማ ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና እነዲወጡም አቶ ማስረሻ ጠይቀዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ በእንኳን ዳህና መጣችሁ ንግግር የሻይ ልማት ክልሉ እምቅ አቅምና ተፈጥሯዊና ስትራቴጂካዊ ጠቃሜታ ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፡፡

በሻይ አመራረት ዘዴ ላይ ለዞን፣ ለወረዳና ለቀበሌ ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለ የአሰልጣኞች ስልጠና መሆኑንም ተናግረዋል።

ክልሉ ከቀረጻቸው ኢንሼቲቮች አንዱ የሻይ ልማት መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት በሻይ አመራረት ላይ ማህበረሰብን በማናቃቀትና በማሳተፍ ተጠቀሚ እንዲሆኑና እንደሀገርም የውጪ ምንዛሬ በማስገባት ረገድ ለክልሉ አስተዋጽኦ በሚያበረክት መንገድ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ስልጠናው ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በሻይ ችግኝ ዝግጅትና እንክብካቤ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *