




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር የማታለም ቸኮል የድጋፍና ክትትል ግብር- መልስ ሪፖርት አቅርበዋል ፡፡
የደጋፍና ክትትል ዓላማው በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ አበረታች ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠልና ጉድለቶችን ፈጥኖ ማረም የሚያስችል አቅጣጫ ማስቀመጥ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
በፖለቲካው፣በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ እና በአስተዳደር ዘርፎች በተከናወኑት ሥራዎች የተመዘገቡ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችንና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ዘርዝረዋል ፡፡
ከፖለቲካ ሥራዎች አኳያ የፓርቲ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የፓርቲ አሰራሮችን በየደረጃው ለሚገኙ አባላትና አመራር ግንዛቤ እንዲያገኙ ከማስቻል አንጻር ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡
በመስኖ ልማት የግብርና ምርትና ምርታማነት ማረጋገጥ የሌማት ትሩፋቶችን፣ ማስፋፋት የአረንጓዴ አሻራ፣ የተቀናጀ የተፋሰስ ሥራዎችና እንሸቲቮችን በየመንደሩ ለይቶ ከማልማት አንጻር እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ውጤታማ በመሆናቸው ተጠናክሮ ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል ፡፡
ሙሉ ፓኬጅ በመጠቀም የኩታ ገጠም እርሻና የሜካናይዜሽን ሥራዎችን በማጠናከር ግብርናን ማዘመን :የተጠናከረ የመረጃ ሥርዓት መዘርጋትና የባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ እንድሁም በየአደረጃው የሚገኙ የፓርቲና የመንግስት አደረጃጀቶች ወጥነት ባለው መለኩ ወደ ተግባር እንዲገቡ ማስቻል በቀጣይ ጊዜያት ትኩረት፠ ከሚሹ ጉዳዮች መካከል መሆናቸውን አመላክተዋል ፡፡
ገቢን የማሳደግ: በጤናው መስክ በሽታ መከላከልና አክሞ የማዳን የጤና ፖሊሲ ውጤታማነት: የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በማጠናከር ጥራት እንዲረጋገጥ ከማስቻል እና በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን ተሳትፎ ከማጎልበት አንጻር የተከናወኑ መልካም ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል አለባቸውም ብለዋል ሪፖርት አቅራቢው ፡፡
በገጠርና ከተማ የሴቶችና የወጣቶችን ሁሉንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ምቹ ዕድሎችን ፈጥሮ ወደ ተግባር ከማሰማራት አንጻር የሚበረታቱ ሥራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መምራት ያስፈልጋል ፡፡
በቀረበው ግብረ-መልስ ሪፖርት ዙሪያ የካፋ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የዘርፉ አመራሮች ሀሣብ አስተያየት ተነስቶ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በጥንካሬ የታዩ ተግባራትን የበለጠ በማጎልበት እንደዚሁም በየአካባቢው የተስተዋሉትን ጉድለቶች ፈጥኖ በማረም መላውን የዞን ህዝብ በሁሉም ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ ሆኖ እንደሚሰሩ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሰዋል ፡፡
