ከ2015 የግብር ዘመን ከደረጃ “ለ”ና “ሐ” ግብር ከፋዮች ከ294 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል ።የክልሉ ገቢዎች ቢሮ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2015 የግብር ዘመን ከደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች በወቅቱና በቅጣት እንዲሁም ከንግድ ዘርፍና ከቤት አከራይ ከደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች እስከ መስከረም 29/2016 ዓ.ም 294 ሚሊዮን 656 ሺህ 341 ብር ከ 49 ሳንቲም መሰብሰብ መቻሉን ገልፆ ይህም ለመሰብሰብ ከታቀደው 71.1 ከመቶ መሆኑን ገልጿል።

ከተሰበሰበው ገቢ 244 ሚሊዮን 921 ሺህ 605 ብር ከ11ሳንቲም በወቅቱ የተሰበሰበ እንዲሁም 47 ሚሊዮን 855 ሺህ 848 ብር ከ79 ሳንቲም ደግሞ በቅጣት የተሰበሰበ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል ።

48ሺህ 122 ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ የከፈሉ ሲሆን 6 ሺህ 538 ግብር ከፋዮች በቅጣት የከፈሉ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል።

በወቅቱ ግብር ያልከፈሉ ግብር ከፋዮች ሳይከፍሉ በቆዩ ቁጥር በየጊዜው ከሚቆጥረው ተጨማሪ ወለድና ቅጣት ሳይዳረጉ አሁንም ቀርበው ግብራቸውን እንዲከፍሉ ቢሮው አሳስቧል።

ቢሮው በወቅቱ ግብራቸውን በመክፈል ለግብር ህግ ተገዥ የሆኑትን ግብር ከፋዮች እያመሠገነ ተገቢውን ግብር በወቅቱ ያልከፈሉ ግብር ከፋዮች ላይ ተገቢውን የግብር ህግ የማስከበር ስራ በመስራት ለክልሉ ህዝቦች ሁለንተናዊ ልማት የሚሆን የፋይናንስ ወረት አሟጦ እንደሚሰበስብ አሳስቧል።ዘገባው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *