ሰንደቅ ዓላማ የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫና መከበሪያና የአንድነታችን መሠረት ነው :-ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 16ኛው የሰንደቅ ዓለማ ቀን ” የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለህብረብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና “! በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች በቦንጋ ማዕከል ተከብሯል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በወቅቱ እንደገለፁት
ኢትዮጵያ ብዙ ቀለማት፣ብሔር ብሔርሰቦችና ህዝቦች የሚገኙባት ሀገር ናት ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በብሔር፣ በጎሳና በቋንቋ ቢለያዩም የጋራ የሚያደርጋቸው በርካታ እሴቶች አሉት ብለዋል።

ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ሰንደቅ ዓላማችን የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ፣መከበሪያና ለሀገር ክብር ብዙዎች የተዋደቁበትና መስዋዕትነት የከፈሉበት ትልቁ መገለጫችን ነው ሲሉም ተናግረዋል ።

የድሮ አባቶቻችን ጠብቀው በክብር ባቆዩት ሰንደቅ ዓላማችን የኢትዮጵያ ህዝቦች ለሀገር ክብር በጋራ የሚቆሙበት፣ለሀገር ዕድገት የሚወያዩበትና ጠላቶቻቸውን በጋራ የሚመከቱበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል።

በበዓሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ ሌሎች የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣የፀጥታ አካላት እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ተገኝተዋል።

በክብረበዓሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ስነስርዓት
አከናውነዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *