ጠቅላይ ሚኒስትርዶ/ር ዐብይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ከየልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን በቻይና ታላቁ የህዝብ አዳራሽ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል::

Spread the love

በሁለትዮሽ ውይይቱ ወቅት ፕሬዝዳንት ሺ በኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ሁነት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንኳን ደስ ያለዎ ብለዋቸዋል::

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነትም ከሁሉን አቀፍ ፅኑ ግንኙነት ወደ ሁኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት (All Weather Strategic Cooperation Partnership) ደረጃ ከፍ ማለቱን ይፋ አብስረዋል:: ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አድንቀው ከቻይናው አረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ጋር ተናባቢ በመሆኑ የግሪን ቤልት እና ሮድ አካል ሆኖ ሊደገፍ እንደሚችል አረጋግጠዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቻይና ኢንቬስትመንት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እመርታ የሚኖረውን አስተዋፅዖ ያነሱ ሲሆን በተለይም በአምስቱ ቁልፍ ምሰሶዎች-በግብርና ማኑፋክቸሪንግ አይሲቲ ማእድን ልማት እና ቱሪዝም ተጨማሪ ኢንቬስትመንት እንዲኖር የማበረታቻ ጥሪ አቅርበዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *