” የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለህብረ ብሄራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን ዋስትና ነው” ! በሚል መሪ ቃል በክልላችን ጥቅምት 5/2016 የተለያዪ ወቅታዊ መልዕክቶችን በማስተላለፍ እንደሚከበር የክልሉ ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ተናግረዋል።
ዋና አፈጉባኤው በዕለቱ የሚከበረው 16ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ እንደሚከበርና ለዚህም አስፈላጊው ዝግጅቶች መከናወናቸውን ተናግረዋል ።
በዕለቱም ሰንደቅ ዓላማችንን በተመለከቱ በተለያዩ ዝግጅቶች ከ 4:30 ጀምሮ እንደሚከበር አፈጉባኤ ወንድሙ ኩርታ አስታውቀዋል ።
