የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ በሆሳዕና ማዕከል ከ’ዕዳ ወደ ምንዳ’ በሚል መሪ ሀሳብ እየተሰጠ በሚገኛዉ ሀገራዊ የአመራር ሥልጠና መድረክ ላይ ተገኝተዋል ፤
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ሆሳዕና ከተማ ሲገቡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ፣ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ክቡር አቶ አደም ፋራህ ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያቀኑት ለብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እየተሰጠ የሚገኘውን ስልጠና ሂደት ለመቃኘት እና በአካባቢው የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት መሆኑ ተጠቁሟል ።
