የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሶስት የቻይና ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሶስት የቻይና ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ።
ሥምምነቱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ከኩባንያዎቹ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተፈራርመውታል።
ሥምምነቱ ከሁለት ፋርማሲዩቲካል እና አንድ በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ ከተሰማራ ኩባንያ ጋር የተፈረመ መሆኑን ኮሚሽነሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
በሥምምነቱ መሰረት ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚሰማሩ ሲሆን፥ ይህም ለኢኮኖሚው ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ኮሚሽነሯ አስታውቀዋል።
ኤፍቢሲ
