በክልሉ አጠቃላይ ሥራዎች ላይ በተደረገው የድጋፍ እና ክትትል ሪፖርት ላይ ያተኮረ ዉይይት እየተካሄደ ይገኛል።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ በብልጽግና ፓርቲና በመንግሥት አጠቃላይ ተግባራት ላይ በተደረገው ድጋፍዊ ክትትል የሪፖርት ግብረ መልስ በቦንጋ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።

ለ15 ቀናት በተካሄደው ክልላዊ የደጋፍና ክትትል ሥራዎች በሁሉም የክልሉ መዋቅሮች እየተከናወኑ ባሉት አጠቃላይ መደበኛ የልማትና የንቅናቄ ሥራዎች ያለበት ደረጃ በድጋፍና ክትትል በጥልቀት መመልከት መቻሉ ተገልጿል።

የመድረኩን አስፈላጊነት የገለጹት፥ የክልሉ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ፥ በድጋፋዊ ክትትሉ በጉድለት የተለዩትን ፈጥኖ ለማረምና በጥንካሬ የሚነሱትን ለማጉላት እንዲሁም ለሌሎች ተሞክሮ ለመቀመር እንደሆነም አስርድተዋል።

ድጋፉ ከሌሎች ጊዜያት በተለየ ሁሉንም መዋቅሮች በማካለል እስከ ብልጽግና ፓርቲ ኅብረትና ቤተሰብ ድረስ መደረጉን የገለጹት አቶ ነጋ፥ በዚህም የብልጽግና ፓርቲ አዲሱን የአባላት አሰራርና ደንብ በተገቢው ከመተግበር አኳያ የተሰሩ ጠንካራ ተግባራት እንዲሁም በመንግሥት ክንፍ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ያለበት ደረጃ በመጎብኘት ህዝባዊ የውይይት መድረክ መፈጠሩን አንስተዋል።

በዚህም በህዝብ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት መኖራቸውንና ቀጣይ በቅንጅት መፍታት በሚቻልበት አግባብ ሁሉም አመራር ወጥ አረዳድ በመያዝ ለቀጣይ ተልዕኮ ራሱን እንዲያዘጋጅ የሚረዳ መድረክ እንደሆነም ነው አቶ ነጋ የጠቆሙት።

የድጋፍና ክትትል ተግባሩ በፓርቲው በተቀመጠው ወጥ አቅጣጫ እንዲሁም የሚጠበቁ ውጤቶችን ከማስገኘት አኳያ የተሳካ እንደነበረ የገለጹት አቶ ነጋ በሚቀርበው ሪፖርት መነሻ መዋቅሮች ያሉበትን ደረጃ በመለየት ለቀጣይ ድጋፍ መሠረት የሚጥል እንደሆነም አንስተዋል።

በመድረኩ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ የክልል አጠቃላይ አመራር እንዲሁም የዞን አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።

መድረኩ ለቀጣይ ኹለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በክልሉ ሁሉም አከባቢ የተደረገው የድጋፍና ክትትል ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *