



በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራው የፓርላማና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የልዑካን ቡድን በኡዝቤኪስታን ታሽከንት ከተማ እየተካሄደ ባለው በ150ኛው በዓለም አቀፉ ፓርላማ ህብረት (አይፒዩ) እየተሳተፈ ይገኛል።
በመድረኩ ኢትዮጵያን በመወከል ንግግር ያደረጉት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር፤ ኢትዮጵያ በህብረቱ ላይ ያላትን አጋርነት አጠናክራ ለመቀጠል ቁርጠኛመሆኗን ገልጸዋል።
ለ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት የሚመለከታቸው አካለት ዓለም አቀፍ ትብብሮችን እንዲያጠናክሩም ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።
